>

“ህወሓት በቆቦ ወረዳ ዳግም በከፈተው ጥቃት ውጊያው ውሃ ቅዳ ፤ ውሃ መልስ ሆኗል....!!!"  (ፋኖ ምስጋን ደስዬ)

 

“ህወሓት በቆቦ ወረዳ ዳግም በከፈተው ጥቃት ውጊያው ውሃ ቅዳ ፤ ውሃ መልስ ሆኗል….!!!”

 ፋኖ ምስጋን ደስዬ

ባልደራስ:


*… መከላከያው የወረራው መረጃ ቢደርሰውም “ውጊያ ወዳለበት ቀበሌዎች ትዕዛዝ ሲደርሰኝ እደርሳለሁ ”የሚል ምላሽ መስጠቱን ሰምቻለሁ

/

“ከሰሞኑን ህወሓት በቆቦ ወረዳ ዳግም በከፈተው ጥቃት 033 መሐጎ እና 022 ወትወት ቀበሌን መልሶ ይዞል” የሚባለው መረጃ ትክክል ነው ወይ? ተብሎ ለተነሳለት  ጥያቄ፣ በራያ ግንባር ከሚንቀሳቀሱት የፋኖ መሪዎች አንዱ የሆነው ፋኖ ምስጋን ደስዬ በሰጠው ምላሽ፣ ” በአካባቢው ቀድሞ የነበረው ሚሊሻ እና ፋኖ ነው፤ነገር ግን እኛ ተገደን ወጥተናል።ከወጣን በኋላ መከላከያው በአካባቢው እንደደረሰ እናውቃለን። ይሁን እንጅ፣ መከላከያው ቢኖርም ፣ ከሰሞኑን የአካባቢው አርሶ አደር ተደራጅቶ እራሱን ከህወሓት ጥቃት እየተከላከለ መሆኑን አውቃለሁ። በትናንትናውየአካባቢው ነዋሪም ለመከላከያው ጥሪ አቅርቦ እንደነበር አውቃለሁ።

መከላከያውም “ውጊያ ወዳለበት ቀበሌዎች ትዕዛዝ ሲደርሰኝ እደርሳለሁ ”የሚል ምላሽ መስጠቱን ሰምቻለሁ።ስለዚህ በቆቦ ውጊያው ውሃ ቅዳ ፤ ውሃ መልስ ሆኖል” ብሏል ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቀው ፋኖ ምስጋን ደስዬ።

“ከዚህ በኋላ በድርድር ስም ወልቃይት እና ራያን ለዳግም ግዞት አሳልፎ የሚሰጠው በአማራ መቃብር ላይ ነው” ሲል በስልክ በሰጠው ቃለ ምልልስ ተናግሯል።

“ የአማራን ህዝብ እና ፋኖን አንገት አስደፋለሁ ብሎ በህግ ማስከበር ሽፋን መንቀሳቀስ አላዋቂነት ነው። ሞትን የናቀ ወጣት በዚህ ደረጃ ማሰብ ከህወሓት አለመማር ነው” ብሏል ፋኖ ምስጋን ደስዬ።

ዘገባው —-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

/

Filed in: Amharic