>

የቤት ውስጥ ባሪያ _ House Negro ...!!! (ዮናስ አበራ ዶ/ር)

የቤት ውስጥ ባሪያ _ House Negro …!!!

ዮናስ አበራ ዶ/ር


*… እራሱን ከሚወደው በላይ ባሪያው ጌታውን ይወደዋል፤ ጌታው ሲታመም “አመመን እንዴ ጌታዬ? Are we sick, my lord?” ብሎ ለጌታው ስፍስፍ ይላል…!!!

“ድሮ ድሮ የቤት ውስጥ ባሪያ (House Negro) የሚባል ነበር።የቤት ውስጥ ባሪያ (House Negro)  ከሌሎች ባሮች ተመርጦ ቤት ውስጥ ብቻ የሚውል ታማኝ አውደልዳይ ባሪያ ነው፤ የሚበላው የጌታውን ትራፊ፥ የሚለብሰው የጌታውን ውራጅ በመሆኑ ተመችቶት ይኖራል።

House Negro (የቤት ውስጥ ባሪያ) ጌታው እራሱን ከሚወደው በላይ ባሪያው ጌታውን ይወደዋል፤ ጌታው ሲታመም “አመመን እንዴ ጌታዬ? Are we sick, my lord?” ብሎ ለጌታው ስፍስፍ ይላል። የጌታው ቤት ላይ እሳት ቢነሳ ከጌታው በላይ ቀድሞ ለማጥፋት ይሟሟታል።

የፊልድ ባሪያ (Field Negro) ጌታው ሲታመም “በሞተ” እያለ ወደ ፈጣሪው ይፀልያል፤ የጌታው ቤት እሳት አደጋ ካጋጠመው ቤቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲነድ ተንበርክኮ ፈጣሪን ንፋስ እንዲልክ ይፀልያል።

በዚህ ዘመን አሳፋሪ የቤት ውስጥ ባሮች አሉን፤ እነዚህ ዘመናዊ ባሪያዎች “መንግስታችን (Our Government)፣ ሰራዊታችን (Our Army)…” ሲሉ ትሰማለህ…. እጅግ አሳፋሪ ነው!”

Malcolm X “House Negro and Field Negro” በሚል በአንድ ወቅት ከተናገረው ዝነኛ ዲስኩሩ ውስጥ የተወሰደ።

በነገራችን ላይ የ Quentin Tarantinoን (ኩዊንቲን ታራንቲኖ) “Django: Unchained” የሚለውን ፊልም ካላየኸው እየው፤ Netflix ላይ አለልህ። ፊልሙ ላይ Steven የሚባለው House negro (Samuel Jackson የሚጫወተው ገፀ ባህሪ) ምን አይነት እርኩስ እንደሆነ በደንብ ትመለከታለህ።

ዛሬ በሃገራችን የቤት ውስጥ ባሮች ነፍ ናቸው!!

በነገራችን ላይ የቤት ውስጥ ባሪያ “Uncle Tom” የሚል ስያሜም ይሰጠዋል። በህክምና “Uncle Tom syndrome” የሚባል የአእምሮ ልክፍት አለ። ስለሱ ፃፍ እንዳትለኝ ብቻ፤ google አድርገህ አንብብ እንጂ።

መልካም ቅዳሜ….

Filed in: Amharic