>

በብልጽግዎች ለኢዜማ አመራርንት የታጩ ብል-ዜማዎች ...!!! (ግርማ ካሳ)

በብልጽግዎች ለኢዜማ አመራርንት የታጩ ብል-ዜማዎች …!!!

ግርማ ካሳ

*…. እስከመቼ ነው የተረኛውና ሸሩኛው ኦህድ እድሜ ዘመን አሽከር ሆነው ከህዝብ ተጣለው የሚቀጥሉት ?????

*… ኢዜማ በብርሃኑ ነጋ አመራርነት ከቀጠለ የትግሉ ጸር፣ የተረኛው ኦህዴድ አጋዥ ነው የሚሆነው፡፡ አምረን ከህወሃጥ ኦህዴድ ያልተናነሰ የምንታገለው ነው የሚሆነው፡፡

ስለዚህ ኢዜማ ውስጥ ያሉ ለሕዝብ የቆሙትን ማገዝ ኢዜማን ከእንጦሮሮስ ማውጣት በቸልታ የሚታይ ጉዳይ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው የኢዜማ ጉዳይ  ለኢዜማዎች ተዉት የሚለው ነገር ተቀባይነት የለውም የምለው፡፡

አባላት፣ መራጮች ሎቢ መደረግ አለባቸው፣ ድምጻቸው የሚያስከትለውን ጥቅም ሆነ ችግር መረዳት አለባቸው፡፡ በማታለል ፣ ላይ ላዩ ጥሩ በሚመስሉ ንግግሮችና ባዶ ተስፋዎች መታለል የለባቸውም፡፡

ለኢዜማ አመራርነት ፉክከር ሶስት 3 እጩዎች ለመሪነት፣ ሶስት ሌሎች እጩዎች ለምክትል መሪነት ቀርበዋል፡፡ ዶር ብርሃኑ ነጋ ከአቶ ዮሐንስ መኮንን ጋር፣ አቶ አንዷለም አራጌ ከአቶ ሃብታሙ ኪታባ ጋር ሆነው ነው እየተወዳደሩ ያሉት፡፡ በኢዜማ ውስጥ፡፡

እነ አንዷእም ኢዜማን በየት አቅጣጫ ለመምራት እንዳሰቡ ሰነድ አዘጋጅተው፣  ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡ ያንን ተከትሎ አቶ ሃብታሙ ኪታባ ፣ “ተፎካካሪዎቻችን (እነ ዶር ብርሃኑ ነጋ) ኢዜማን ወዴት እንደሚወስዱ እየጠበቅን ይኸው 3ኛ ቀኑ ነው፡፡ አሁንም እንጠብቃለን” የሚል አስተያየት በመስጠቱት ተፎካካሪዎች ቻሌንጅ አድርጓል፡፡

ይህ ጥያቄ ተገቢና መሰረታዊ ጥያቄ ነበር፡፡ ነገር ግን የዶር ብርሃኑ ምክትል፣  አቶ ዮሐንስ መኮንን አንድ አስቂኝና አስገራሚ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ኢዜማ እድር ወይንም የግል ማህበር፣ ወይም ክለብ አይደለም፡፡ ኢዜማ የፖለቲካ ፕርቲ ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ ከሕዝብ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ አባላት የድርጅታቸውን አመራሮችም ሲመርጡ ሕዝብ ምን ይላል የሚለውን ከግምት ማስገባት አለባችው፡፡ ለኢዜማ ድርጅት የሆነው ሕዝብን ይዞ ለውጥ ለማምጣት ከሆነ ከህዝብ ጋር ያለው ግንኙነት እንደ ቀላል ነገር ተንቆ የሚተው ነገር አይደለም፡፡ ፌስ ቡክ የሕዝብ ሜዲያ ነው፡፡ ወደ ሕዝብ መድረሻ አንዱና ትልቁ መንገድ ነው፡፡

“የኢዜማ አመራር ምርጫ ወሳኞች በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ ከ400 በላይ የምርጫ ክልሎች (ወረዳዎች) ተወክለው የሚመጡ የጉባኤ ተሳታፊዎች ናቸው”  ያለው አቶ ዪሐንስ፣ የዶር ብርሃኑ ነጋ ምክትል፣ “የምርጫ ሰነዳችንንም ለፌስቡክ ሳይሆን ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከታቸው ኢዜማውያን በራሳችን እቅድ እና መንገድ እናቀርባለን” ሲል ከ400 መቶ አባላት ውጭ ላለው ለተቀረው ኢትዮጵያዊ ግድ አይሰጠንም የሚል አይነት ምላሽ ነው የሰጠው፡፡

አቶ አንዷለም አራጌ ቢቢሲን ጨምሮ ከተለያዩ ሜዲያዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡ ከህዝብ የተደበቀ ምንም ነገር ስለሌለው፡፡ ግልጽነት ባለው መልክ  ነው፣ ከህዝብም ሆነ ከሜዲያ የሚነሱ ጥያቄዎችን እየመለሰ ያለው፡፡ ከሕዝብ የሚደብቀው ፣ በሴራ ፣ ከበስተኋላ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ ዶር ብርሃኑ ነጋ ፣ ልክ እንደ አለቃው ዶር አብይ አህመድ፣ ጋዜጠኞች መድፈር እየተሳነው የመጣ ሰው ነው፡፡ ከሜዲያዎች ለቃለ መጠይቆች ጥሪ ቀርቦለትም፣  ኢዜማን በየት አቅጣጫ መምራት እንደሚፈልግ ለመናገር ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ምን አልባት በፋና፣ ዋልታ፣ ኢቢሲ፣ OBN በመሳሰሉት ፣ ይችን ያችን ጠይቁኝ ብሎ ቃለ ምልልስ ሊይደርግ ይችል ይሆናል፡፡

በኔ እምነት እነ አቶ ዮሐንስና ዶር ብርሃኑ  ነጋ፣  ከአብይ አህመድ ጋር የተቆራኙ ስለሆነ፣ ነገሮችን ሸፋፍነው፣ ደባብቀው፣ ባዶ ተስፋ እየሰጡ ፣ 400 አባላት ያሏቸውን ውስጥ ውስጡን፣   በገንዘብም ይሁን  በብልጽግና  ደህንነቶች በኩል በማስፈራራት እንዲመርጧቸው የመስራት ስራ ለመስራት አስበው ይሆናል፡፡ በርግጥ ለህዝብ የሚጠቅም ሃስብ ካላቸው፣ ምን ያስፈራቸዋል ለህዝብ ይፍ ለማድረግ ???????  አዎን መራጮች አባላት ናቸው፡፡ ግን  መራጮች የህዝብ አካል አይደሉም እንዴ ? ኢዜማ አዳዲስ አባላት እንዲኖሩት አይፈለግም እንዴ ? ኢዜማ የጥቂት ግለሰቦች እድርና ማህበር ብቻ እንዲሆን ነው እንዴ የሚፈለገው ????? ግልጽነት፣ ሕዝባዊነት የሚባሉ ትላልቅ እሴቶች የኢዜማ እሴቶች አይደሉም  እንዴ ? ነገሮች እየተደባበቁ፣ በሴራ፣ ውስጥ ውስጡ መንቀሳቀስ፣ በግንቦት  ሰባት የነበረው አይነት፣ የሴራ፣ የማታለል፣ የማዘናጋት ፖለቲካ  አዋጭ ፖለቲካ ነውን ?

በኔ እምነት እነ አቶ ሃብታሙ ኪታባ ከነ ዶር ብርሃኑ ኢዜማን በየት አቅጣጫ መምራት እንደሚያስቡ መጠበቅ የለባቸውም፡፡ ያለፈው ሶስት አመቱ አካሄድ እንዲቀጥል ነው የሚፈልጉት፡፡ ኢዜማ የብልጽግ ና አሽከር፣ ተደማሪ ተለጣፊ፣ ተጋላቢ ሆኖ እንዲቀጥል ነው የሚፈልጉት፡፡ ኢዜማ እውነተኛ ተቃዋሚ፣  ለሕዝብ ተስፋ የሚሆን ፓርቲ ሳይሆን የብልጽኛ አጋር ታናሽ እህት ሆና እንድትቀጥል ነው የሚፈለጉት፡፡ ለኢዜማ አመራርነት በብልጽኛዎች የታጩ እጩዎች ናቸው፡፡

Filed in: Amharic