>

አዲስ አበባ ሆይ! የጎንደር እጣ እንዳይገጥምሽ እርሱ ይጠብቅሽ...!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

አዲስ አበባ ሆይ! የጎንደር እጣ እንዳይገጥምሽ እርሱ ይጠብቅሽ…!!!

ጌታቸው ሽፈራው


*….  የውሃብያው ቡድን በቅርቡ አዲስ አበባ ስታዲዬም የቁርአን ውድድር እናደርጋለን እያሉ ነው። አዝማሚያው ሲታይ የተፈቀደላቸው አይመስልም። ተፈቀደላቸውም አልተቀፈቀደላቸውም ግን እነሱ ለሰይጣናዊ አላማቸው ይጠቀሙበታል…!!!

ጎንደር ከተማ ክፉ እቅድ ታቅዶባት ነበር። የውሃብያው ቡድን በጎንደር  የጎዳና ላይ አፍጥር ላይ ችግር እንዲፈጠር በማድረግ ጎንደርእንደ ከተማ፣ አማራን እንደ  ሕዝብ ስም ሊያጠፋ ነበር። የጎንደር ጎዳና ላይ አፍጥር ባለመሳካቱ ሌላ እቅድ ሲፈልጉ፣ ቀብር አለ ተባሉ። የቀብሩን ስነ ስርዓት ተጠቀሙበት። አሁንም ራሳቸው በፈጠሩት ችግር ጎንደርን ይወቅሳሉ። አማራን ይረግማሉ።

አዲስ አበባ የጎንደር አይነት እጣ እንዳይደርሳት ያሰጋል። በአዲስ አበባው አፍጥር ላይ ችግር ተፈጥሯል። ከዛ ቀደም በለሚኩራና ሌሎች አካባቢዎች ችግር ፈጥረዋል። ተማሪዎች ትምህርት ቤት ውስጥ ካልሰገዱ ብለው ጩኸት ላይ ከርመዋል። ይህን ሁሉ ያደረጉት ከእነ ሙፍቲ ቀድመው መሪ መስለው ለመያተት ነበር። ሕዝብን ለመቀስቀስ ይጠቅመናል በሚል ነበር።

አዲስ አበባ ሌላ ተመሳሳይ ችግር እየመጣባት ነው። በቅርቡ አዲስ አበባ ስታዲዬም ላይ ውድድር እናደርጋለን እያሉ ነው። አዝማሚያው ሲታይ የተፈቀደላቸው አይመስልም። ተፈቀደላቸውም አልተቀፈቀደላቸውም ግን እነሱ ይጠቀሙበታል። ከተፈቀደላቸው ውድድሩን በሰላም እንዲጠናቀቅ አይፈልጉም። ችግር ተፈጥሮ ዜና እንዲሆን ይፈልጋሉ። ተጋባዦች ከግብፅ ጨምሮ ይመጣሉ ስለተባለ ዜና ያደርጉላቸዋል። የኢትዮጵያ ሙስሊም እየተጠቃ ነው ለማለት ነው። ይህ ሁሉ በደል እየተፈፀመ ዓለም እያገዘን አይደለም ለማለት ነው። ለዚህ ፕሮፖጋንዳ ሲባል ችግር ይፈጥራሉ።

ከተከለከሉ ደግሞ ተከለከልን ብለው ያስጮሁታል። ከሁሉም አደገኛው ግን ፕሮግራሙ ላይ ሆን ብለው ችግር ፈጥረው የአዲስ አበባንም የኢትዮጵያንም ስም ካጠፉ ነው። ያደርጉታል።

የውሃብያው ቡድን  ከትህነግ ጋር አላማ ተጋሪ ሆኗል። ትህነግ ለኢትዮጵያ ቱርክና የአረብ አገራት ወታደራዊ እገዛ እያደረጉላት ስለሆነ ይህ ግንኙነት መበላሸት አለበት  ብሎ ያምናል። ይህ ፕሮግራም ላይ ችግር ቢፈጠር አረብ አገራት ያልሆነ ስዕል ይይዛሉ። ባለፈው የጎንደሩ ችግር ቱርክ መግለጫ እንድታወጣ አድርገዋል። ስለሆነም ለትህነግ ምቹ አጋጣሚ ነው። ኢትዮጵያን  ከአረብ አገራትና ከቱርክ ጋር አቆራርጥበታለሁ ብሎ ያስባል።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ካላሰበበት አዲስ አበባንም ኢትዮጵያንም ስማቸውን ያስጠፋል። ለትህነግ እድል ይሰጣል። መንግስቱስ መሰል ችግርን ሊቀርፍ አይችልም። ንፁሃንን እያሰረ አሸባሪ የሆነውን የውሃብያ ቡድን የሚያባብል መንግስት ነው። ማለት የምንችለው አዲስ አበባ ሆይ የጎንደር እጣ አይግጠምሽ ነው! አዲስ አበባ ከጎንደር እጣ መዳን የምትችለው ይህን ጉዳይ ቀድሞ መረዳት የሚችል አካል ቢኖር ነበር። እውነተኛዎቹ ሙስሊሞች ውሃብያው ከመቸ ወዲህ ቁርአንን ያውቀዋል ይላችኋል። የውሃብያው ቡድን ቁርዓን ውድድርን ለእምነት አይጠቀምበትም። ለፖለቲካና ለብጥብጥ ነው። አዲስ አበባ ይህ አደጋ ተደቅኖባታል። ጎንደር ላይ በጎዳና ላይ አፍጥር ሰበብ አድርገው እንደፈፀሙት አዲስ አበባ ላይ ደግሞ በቁርአን ውድድር ስም ሌላ ችግር ሊፈጥሩ ነው።

Filed in: Amharic