>

“ፋኖ የመንግሥት ሚሊሻ መሆን አይችልም...!!!"  (ሻለቃ ፋሲል ገበየሁ - በደልጊ የአማራ ፋኖ አዛዥ )!!

“ፋኖ የመንግሥት ሚሊሻ መሆን አይችልም…!!!” 

ሻለቃ ፋሲል ገበየሁ – በደልጊ የአማራ ፋኖ አዛዥ !!


*…. በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፤ ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማ እና አካባቢው በጦር ግንባር ከሕወሓት ጋር ሲፋለሚፈሙ የከረሙ ፋኖዎች እየተሳደዱ ነው!!!

በደልጊ ከተማ  ዋኘው ፣ ጌጡ ፣ በቃሉ እና ኃይማኖት የተባሉ ፋኖዎች በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እያሉ ከተማ ውስጥ ተከበው ታስረዋል።  ከደልጊ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ድኩር አርባ ከተማ ፋኖ አያናው እና ፋኖ ገነቱ እየተሳደዱ ነው። በርካቶች ደግሞ ከተሞችን ለቀው ወደ ጫካ ከገቡ ሰነባብተዋል።

አገዛዙ በፋኖ ላይ የሚያደርገውን የማሳደድ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ያሰራቸውን ፋኖዎችም ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ የአማራ ፋኖ በደልጊ አዛዥ ሻለቃ ፋሲል ገበየሁ አሳስቧል።

“ፋኖ ወንጀለኛ አይደለም። ከእኔ ውጭ የታጠቀ ኃይል መኖር የለበትም ብሎ መንግሥት እያሳደደን ያለው። ፋኖ ግን የመንግሥት ሚሊሻ መሆን አይችልም” ብሏል ሻለቃ ፋሲል።

ሕወሓት ለዳግም ወረራ በራያ ቆቦ እና በወልቃይት ጠገዴ በኩል ለመምጣት እየተዘጋጀ እንደሆነ የገለፀው ሻለቃው፣ “ጁንታ ቢመጣ እኛን አልባ ሊመለስ አይችልም” ብሏል።

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Filed in: Amharic