>

ለ46 ቀና በዕስር ላይ የቆየው  የባልደራሱ ቢኒያም ታደሰ  ለተጨማሪ 7 ቀናት ተቀጠረ...!!!

ለ46 ቀና በዕስር ላይ የቆየው  የባልደራሱ ቢኒያም ታደሰ  ለተጨማሪ 7 ቀናት ተቀጠረ…!!!

ጌጥዬ ያለው


*…. በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የ8ሺ ብር ዋስትና ተፈቅዶላቸው የነበሩ ከፊል የባልደራስ አባለት፣የፖሊስን ይግባኝ ተከትሎ የከፍተኛ ፍ/ቤቱ የዋስተና ብይኑን በመሻር ለተጨማሪ 16 ቀናት በእስር እንዲቆዮ መወሰኑ ይታወሳል።

በጎንደር ቨተከሰተው ብጥብጥ አዲስ አበባ ሆነህ ተሳትፈሃል በሚል በደህንነቶች የታፈነው ቢኒያም ታደሰ ለ46 ቀናት በማዕከላዊ እስር ቤት እየተሰቃየ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ወጣት ቢኒያም ቀርቦ ነበር።  ፖሊስ “አሁንም መርምሬ ያልጨረስኩት ሰነድ አለ፤ ስለሆነም ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ይፈቀድልኝ” በማለት አቤቱታ አቅርቧል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው፣ ፖሊስ ላለፋት 46 ቀና ምንም ዓይነት የምርመራ ውጤት ሳያቀርብ፣ ዛሬም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ ችሎቱን መናቅ መሆኑን አስረድተው፣ ቢኒያም የዋስትና መብት እንዲፈቀድለት ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍ/ቤት፣ የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሎ ከተጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ 7ቱን በመፍቀድ ለሰኔ 12 መዝገቡን ቀጥሮታል።

በተያያዘ ዜና ግንቦት 22/2014 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የ8ሺ ብር ዋስትና ተፈቅዶላቸው የነበሩ ከፊል የባልደራስ አባለት፣የፖሊስን ይግባኝ ተከትሎ የከፍተኛ ፍ/ቤቱ የዋስተና ብይኑን በመሻር ለተጨማሪ 16 ቀናት በእስር እንዲቆዮ መወሰኑ ይታወሳል።

ወሳኔውን ተከትሎ የተከሳሽ ጠበቆች የተፈቀደው የጊዜ መጠን የተጋነነ በመሆኑ እንዲስተካከል ለፊደራሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር።

ለአቤቱታው ለዛሬ ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም፣ ሳይሳካ ቀርቷል።በመሆኑም፣ ለሰኔ 7/2014 ከቀኑ በ8 ሰዓት በድጋሜ ተቀጥሯል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ እስረኞች፣ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን አቤቱታ አቅርበዋል።

Filed in: Amharic