>

አብይ ኢሳያስና የደደቢቱ ዘንዶ....!!! (ኦሀድ ቢንአሚ)

አብይ ኢሳያስና የደደቢቱ ዘንዶ….!!!

ኦሀድ ቢንአሚ


የዛሬ አራት አመት ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ አንድ የኬንያ ጋዜጣ ካርቱኒስት ወያኔን ከአራት ኪሎ ለማስወጣት ያደረጉትን ተጋድሎ በዚህ መልክ አስቀምጦት ነበር፡፡ የዘንዶው አናት ላይ ጦራቸውን ሲሰብቁበት በሚያሳይ ስዕል ነበር የገለጸው፤ ከዛ ከታች “አሁን ከባዱ ስራ ይጠብቃቸዋል፤” ይላል፤ ወያኔን ከአራት ኪሎ ከማስወጣት ይልቅ የድርጅቱን መርዛማ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ መዋቅር በተለይም ከትግራይ ስነልቦና ቆራርጦ ማውጣት የከበደ እንደሚሆን ተናግሮ ነበር ካርቱኒስቱ፤

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ወደ ኤርትራ ባቀኑበት ወቅት በተደረገላቸው የእራት ግብዣ ላይ የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂም ስለቀጣዩ ምዕራፍ ሲናገሩ ቀጣዩ ምዕራፍ “ቀላል አይሆንም፤ እኛ ግን ከጎንህ ነን በርታ፤” ብለው ነበር፤ እነሆ የጠ/ሚ አብይ አህመድ መንግስት ከተመሰረተ ጀምሮ ከፍተኛውን አደጋ የጋረጠው ይሄው ኬንያዊው ካርቱኒስት በዘንዶ የመሰለው ወያኔ ነው፤

አብይ የዘንዶውን አናት ጦራቸውን እንደሰበቁበት በግልጽ የሚታይ ሆኖ የትግራይ ዋሻ ውስጥ ከተደበቀ አራተኛ አመቱን አስቆጥሯል፤ ዘንዶው የነደፋቸውም የዘንዶውን መርዝ በአገሪቷ ላይ የመርጨት ተልዕኮአቸውን እየተወጡ ነው፤ እድል ቢያገኝ አብይንም ኢትዮጵያንም ከመዋጥ ወደኋላ የማይለው ዘንዶ አሁን መልኩን ቀይሮ ልዑካኑን ወደ አሩሻ (ታንዛኒያ) ለመላክ ዝግጅት እያደረገ እነደሆነ እየተወራለት ነው፡፡

አብይ ከዘንዶው ጋር የጀመሩትን ግብግብ የመጨረሱ ተግባር ጥቂት ምዕርፎች ቀርተውታል፤ ዘንዶው ከአቅሙ በላይ ጠላቶች ፈጥሯል፤ ፍጻሜውን ሕዝብ ሳያስጨርስ ቢቀበል መልካም ነበር፤ ትግሉ መልኩን ቀይሮ ይቀጥላል፤ ዘንዶው ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሚኖረው ቀጣይነት መርዛማ ከመሆን ውጭ ምንም የሚፈይደው ነገር የለውም፤

ዘንዶው የነደፋቸው መርዛቸውን ከማስተላለፋቸው በፊት ራሳቸውን ቢያክሙ ጥሩ ነው፡፡

Filed in: Amharic