>

እቡይነት፣ እኩይነትና ቅጥፈት ወንበርና መዋቅር ይዘው በገሐድ ተከሰቱ...!!! (ይሁኔ አወቀ)

እቡይነት፣ እኩይነትና ቅጥፈት ወንበርና መዋቅር ይዘው በገሐድ ተከሰቱ…!!!

ይሁኔ አወቀ


*….. ስለ ስንቱ …የምናውቀው ደረቅ እውነት ዘብ ቆመን… ስለ ቁልሉ ቅጥፈታቸውስ መልስ ሰጥተን እንዘልቃለን…???

የማናልፈው ግን፣ በፋኖ ላይ የሰነዘሩት አይን ያወጣ የፈጠራ ክስና ፍረጃ ነው፡፡  እርሳቸው የጠቀሱትን ሁሉ ወንጀል የፈጸመው… በእርሳቸው የደህንነት ተቋም የሚመራው የፋኖን ስም ለማጠልሸት  ሆነ ተብሎ ተቋቁሞ  በአምሓራ ምድር የተሰማራው ስውር ታጣቂ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን…  በፋኖ ስም በምድር ላይ ያለ ሁሉ ወንጄል በዚያ ቀዬ እንዲፈጽም አቅጣጫና ቀለብ የሚቋጥርለት ራሱ ተረኛው ኃይል ነው፡፡ ይህ ቡድንን አስቀድመው ያስፈረጁት በኦሮሚያ ክልል መንግስት መሆኑን ያስታውሷል፡፡  ለዚህ ቀን ክስ ሲባል ደግሞ…  በፋኖ ስም በወሎ ምድር ዝርፊያ ፈጽሟል፣ በጎንደር መስጊድና ቤተ ክርስቲያን አቃጥሏል፡፡ በጎጃም… ህዝብን እያሸበረ ንብረት ቀምቷል፡፡ ዋናው ፋኖ ለዚህ አኩይ ድርጊት በወቅቱ  በመግለጫ መልስ ሰጥቷል፡፡ በታጋይ ፋኖ ዘመነ ካሴ የሚመራው የአምሓራ ህዝባዊ ኃይል  ‹‹እነዚህን አደገኛ ኃይላት የምንታገለው እኛ ነን›› ብሏል፡፡ ታዲያ ዘመንን የሚሳድደው ኃይል… ዘመነ… አሸሽ ደለለ? ዘመነ፣ ፎርጅድ ብር አተመ ብሎ ነውን?  ምሬ ወዳጆ… ሴት ደፈረን? ጉዳዩ ወዲህ ነው፡፡ ሁሉንም የፈጸመው የኦሮሙማ ሃይል… አዳፋውን ለፋኖ በማሸከም… ሊጸዳዳ ፈልጓል፡፡ ፋኖን ከወያኔ በላይ በህዝብ የማስጠላት መንገዱም… በድብቅ የተጀመረ… ዛሬ በፓርላማ የተገለጸው ነው፡፡

መከላከያ በወያኔ… የተፈጸመበትን ክህደት  ዘንግቶ ፊቱን ወደ ፋኖ እንዲያዞር ለማድረግ… አብሮት በምሽግ የተዋደቀውን “ፋኖ” ‹‹መሳርያህን ቀምቶሃል›› ሲሉ… ጠላት ሊያስነሱበት ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን፣ ያን ጥቁር ክላሽ  ወያኔ ከመከላከያ… ፋኖ  ደግሞ ከወያኔ ማርኮ እንደታጠቀው አደገኛው ሰው አጥተውት አይደለም፡፡ ፋኖን እና የአምሓራ ኃይላትን ለማጥፋት ቆርጠው ስለተነሱና የአምሓራን ህዝብ ጥያቄ ለማዳፈን ካላቸው እኩይ ድብቅ አላማ አንጻር ፋኖ ስለሚያስፈራቸው  ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን አይችሉም፡፡ ነገ… እኛ ብናልፍ እንኳ… ፋኖ የፈረጀውን አካል በካቴና አስሮ ለፍርድ የሚቀርብበት ቀንን በክንዱ ያመጣል፡፡

ይገርማል!!!

በመሪዎች ታሪክ… ፓርላማ ላይ ግጭት የቀሰቀሰ መሪ ቢኖር ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ብቻ ይመስለኛል!!!

‹‹ያለ ህዝብ ነጻ ፈቃድ  በኦሮምኛ መዝሙር በት/ቤቶች በግዳጅ… በፈጸሙ ትክክል አይደለም ›› ሲል ድምጽ ያሰማ ሁሉ… የኦሮሞ ህዝብ ጠላት እንደሆነ… ነግረውናል፡፡  ኦሮሚያን… እንደ ሉዓላዊ ሀገር… ከቱርክ፣ ከፈረንሳይ፣ ከጣልያን ጋር እያወዳደሩ ተሳልቀውብን ወጥተዋል፡፡ በኦሮሚያ ት/ቤትና ኢንባሲ ይኄን ማድረግ ካስፈለጋቸው ቢያደርጉስ ማን ከለከላቸው? ይህ ግን፣ ራስ ገዝ ከተማ፣ ወይም ከኦሮሚያ ውጭ የሆነ ራሱን የቻለ ወኪል ያለው መስተዳድር መሆኑን አላጡትም፡፡ ጀርባዉ ሌላ ነው፡፡ ቱርኮች በቱርክ ትምህርት ቤት እንጂ… በከተማዋ እየዞሩ የጥላቻ መርግም የተጫነው መዝሙር አዲስ አበቤ እንዲዘምር አላስገደዱም፡፡

ይህን ድርጊት የተቃወመውን “ባልደራስን”  ፓርቲ ‹‹የኦሮሞ ህዝብ ጥላቻ ያለው›› ሲሉ… ለጥቃት እንዲመቻች ወንበራቸውን ተጠቅመው ለሚዘውሯቸው አፋኝና ገዳዮች መልዕክት አድርሰዋል፡፡ ያሳዝናል፡፡

ኢትዮጵያ  ነጻ የፍትህ ተቋምና “ህግ” ቢኖራት ኖሮ… ግጭት ቀስቃሽና ህዝብን ከህዝብ ለማናከስ፣ ቡድንን ከቡድን ለማጠፋፋት፣ የዘር ፍጅት  በመፈጸምና ለማስፈጸም…  ህዝብ የሰጠው ስልጣኑን ተገን በማድረግ የጥላቻ ቅስቀሳና ንግግርን በማር ለውሶ የነዛ አደገኛው ሰው ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ  ለፍርድን ታቀርበው ነበር፡፡

ታዲያ ምን ያደርጋል…! ለባለ ዙፋኑ… ተረኛው አንባገነን ህጉ አይሰራም!! ይከሳል እንጂ… አይከሰስም፣  ያስራል እንጂ… አይታሰርም! !! ‹‹ … ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ….››

ፋኖን በጠላትነት ለማስፈረጅ የሄደበት እኩይ መንገድ…  ሰይጣንን ያስንቃል፡፡  የምናውቃቸውን ንጹሓን ከችሎት ቀድሞ ለመፈረጅ የተጠቀመበት ቃል… የመንደር አሉባልተኛን ያስከነዳል፡፡ ህግ  መረጃ አጥቶ ንጹሓን እንደሆኑ አምኖ የለቀቃቸውን… ዜጎች ሰውዬው ያለ አንዳች ሐፍረትና በድርቅና ሲወነጅልና ሲፈርጅ ፊቱ ቅጭም አይልም፡፡

ሰይጣን ራሱ ‹‹እኔን የሚያስንቅ መጣ›› ብሎ የሚቀናበት ይመስለኛል፡፡  ‹‹ቤንዝንነና ገጀራ አስይዞ በመሰጊድ ላይ ቃጠሎ እንዲፈጸም አሰማርቷል›› ሲል የከሰሰው ኦሮሙማ አመት ከ6 ወር አስሮ መረጃ ሲያጣ ያለ አንዳች ይቅርታ እንደፈታው አልረሳንም፡፡ አብይ አደገኛው ዘረኛ ሰው ለመሆኑ መረጃ አትፈልጉ… በዚህ ፓርላማ መረጃ ሰጥቷል፡፡

‹‹ተረኝነትን አቁሙ… .›› ኢ ፍትሓዊነትን ና ከህዝብ ፈቃድና ጥያቄ ውጭ  በአንባገነንነት በጉልበት የምትፈጽሙት ስህተት ነው›› ካልክ… አንተ የኦሮሞ ጠላት ነህ!!! ሲል ይፈርጅሃል፡፡

የፓርላማው ውሎ የነገረኝ አንድ እውነት ነው!!!

አምሓራ እና ኢትዮጵያውያን ከአሁኑም የከፋ  ጊዜ ከፊታቸው እንደሚጠብቃቸው ነው፡፡ ጠቅላያችን ትላንት ላፈሰሱትም  ደምም ሆነ አሁን እየሰሩት ላለው እኩይ ስራ  ሽልማት እንደሚገባው ዛሬም ሊነግሩን ሲዳዱ ከማዬት በላይ የእለተ ምጽዓት መቃረብ ማሳያ ምን ይኖራል?

ህግን የምትተማመን ዜጋዬ ውሃ በልቶሃል!!!

ሰውዬው…” ህግ ማለት” ራሱና የራሱ ጎሳ አባላት ብቻ እንደሆኑ የሚያስብ መርዘኛና ዘረኛ ሰው ነው፡፡

ከዚህ ሰው የጽሞናና ጊዜ፣ የተስፋ ዘመን የምትቃትት ፈሪ ካድሬ ሆይ እርምህን አውጣ!!!

ነጋችን ይበልጥ አስፈሪ ነው!!! አንባገነናችንን በይፋ አዋልደናል!!!

አንተ የአፍሪካው ስመ ጥር  አንባገነን ኤዲ አሚን ዳዳ ሆይ…! የሚያስንቅህ ህጻን ተወልዷልና አይክፋህ!!!

Yihune Awoke

Filed in: Amharic