>

"እኛ ብዙ ነን እና ከትግሬ ጋር አታወዳድሩን" :- ልብ ሰባሪዉ የአቢይ አህመድ ቃለ መጠይቅ (ሸንቁጥ አየለ)

 

“እኛ ብዙ ነን እና ከትግሬ ጋር አታወዳድሩን”

 :- ልብ ሰባሪዉ የአቢይ አህመድ ቃለ መጠይቅ

 

ሸንቁጥ አየለ


የጎሳ ፖለቲካ እጅግ እደገኛ ካንሰር መሆኑን ከመለስ እና ከአቢይ መልስ ማዬት ይቻላል!!!

የመለስ ዜናዊን እና የእቢይ እህመድን ነጽሮተ አለም ከተወሰኑ ቃለመጠይቆቻቸዉ በማዬት ብቻ የጎሳ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ላንዴና ለመጨረሻ ስሩ ተቆፍሮ ተነቅሎ ካልተቃጠለ ኢትዮጵያዉያን በፍጹም እንደ አንድ እኩል ነጻ እና ፍትህ የተላበሰ ህዝብ አብረዉ ሊኖሩ እንደማይችሉ ግልጽ ነዉ፥፥

ኢትዮጵያዉያን እኩል ህዝብ እንዳይደሉ የተናገረበት ልብ ሰባሪዉ የአቢይ አህመድ ቃለ መጠይቅ በስፋት ቢተነትን የጎሳ ፖለቲካ ለአንዲት ሀገር እንዴት ካንሰር እንደሆነ ብዙ የሚነግረን ነገር አለ፥፥

—————————

1== መለስ ዜናዊ ” የህዉሃት/ኢህ አዴግ መንግስት ለትግራይ ብሄር ያደላል፥፥ ንግዱንም፥ መስሪያ ቤቱንም ስልጣኑንም ፥ ልማቱንም የተቆጣጠረዉ የናንተ ብሄር ብቻ ሆነ” ተብሎ ሲጠዬቅ  ይመልስ የነበረዉ ” ትግራይ በጦርነት የተጎዳ ክልል ስለሆነ ከሌሎች ብሄሮችና ክልሎች ጋር አታወዳድሩት ይላል፥፥

— እንደሚታወቀዉ ህዉሃት ስልጣን ላይ በነበረ ሰኣት በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የሀገሪቱ ከተሞች ያሉ ሆቴሎች እና ቡና ቤቶች በግዳጅ የትግርኛ ዘፈ ን እንዲከፍቱ ይደረጉ ነበር፥፥

2==አቢይ አህመድ ደግሞ  “ተረኝነት አለ፥፥ንግዱንም፥ መስሪያ ቤቱንም፥  ስልጣኑንም ፥ ልማቱንም የተቆጣጠረዉ የናንተ ብሄር ብቻ ነዉ፥፥ ከናንተ ብሄር ወንጀለኞች ሌሎች ብሄሮችን ጨፍጭፈዉ እና ብዙ ወንጀል ሰርተዉ እየተሾሙ እየተሸለሙ ይኖራሉ” ተብሎ ሲጠዬቅ  የመለሰዉን መልስ የአማርኛዉ ዘርፍ ቢቢሲ ተገርሞ እንደሚከተለዉ ዘግቦታል

“የኦሮሞ ህዝብ 35 በመቶ መሆኑ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ማነጻጸር እንደማይገባና …….።”

ሚሊዮኖች በኦነግ ሸኔ ሲጨፈጨፉና ሲፈናቀሉ አቢይ አህመድ የሚሰጠዉ ምላሽ “በህዉሃት ጊዜ ይሰራ የነበረዉ እናሳ ቁጥር ባለዉ ሀይል ስለሆነ ወንጀል ነዉ ፥፥ አሁን ግን ብዙ ቁጥር ባለን ወገኖች የሚሰራዉን ወንጀል ከትግሬ ጋር አታወዳድሩን፥፥ እኛ ብዙ ነን እና ከትግሬ ጋር አታወዳድሩን” በማለት መሆኑ ነዉ፥፥ ከዚህ በላይ ተረኝነትና ዘመነኝነት ምን አለ፥፥

ይባስ ብሎም ሳያፍር 15 ሚሊዮን ዜጎች የሚኖሩበት አዲስ አበባ ላይ ኦሮሚያ የሚባለዉ የተረት ተረት ክልል መዝሙር በግድ ሊዘመር ይገባዋል፥፥ ይሄ መዝሙር እንዳይዘመር መፈለግ ኦሮሞ ጠልነት ነዉ ሲል ማብራራቱን ቢቢሲ በትዝብት መልክ ዘግቦታል፥፥

———–,

ኢትዮጵያዉያን እኩል ህዝብ እንዳይደሉ የተናገረበት ልብ ሰባሪዉ የአቢይ አህመድ ቃለ መጠይቅ በስፋት ቢተነትን የጎሳ ፖለቲካ ለአንዲት ሀገር እንዴት ካንሰር እንደሆነ ብዙ የሚነግረን ነገር አለ፥፥

https://www.bbc.com/amharic/articles/ced221n74qpo

Filed in: Amharic