>

ስብሀት ነጋ እንዲፈታ እጅ ያወጣና የደገፈው  ብርሀኑ ነጋ ኢዜማን ሊመራ አይገባም...!!!" (አበበ ቀስቶ)

ስብሀት ነጋ እንዲፈታ እጅ ያወጣና የደገፈው  ብርሀኑ ነጋ ኢዜማን ሊመራ አይገባም…!!!”

አበበ ቀስቶ

 

 ፕ/ር ብርሀኑ ነጋን የምንሞግተው በማስረጃ ነው።

ስብሀት ነጋ ሲፈታ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በወቅቱ ጉባ ላይ በተካሔደ የሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባ ላይ ይሁንታ መስጠቱንና ሳይቃወም የተስማማ ሰው መሆኑን ደጋፊዎቹ ምን ብለው ያስተባብሉ ይሆን ??

ይህን አስመልክቶ  ከውጭ አገር ለገና በዓል ለመጡትና ዶላር ከፍለው የቤተመንግስት እራት ለበሉት ዲያስፖራዎች በአንደበቱ በአደባባይ

ሶስቱም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ገና መጀመሪያ በመርህ ደረጃ  እስረኛ ይፈታ ብለን ስንወስንም በሁዋላም ለአባይ ጉብኝት ሔደን በጉባ ባደረገግነው ስብሰባ ላይ

በዐቃቢ ሕግ የሚፈቱ ተብሎ ስምዝርዝር ቀርቦልን የስብሀት ነጋንና የሌሎች ተፈችዎችን ፍቺ በጋራ ነው የወሰነው ሲሉ አስረድተዋል።

      ስለዚህ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ስልጣን ያግኝና ያገኘውን ስልጣን አይጣ  እንጂ መለስ ዜናዊንም ከሞት ቀስቅሰው ከመቀስቀስ አይመለስም። እናም ይህ ሰው  ኢዜማን በታማኝነትና በብቃት የመምራት ብቃት የለውም።

Filed in: Amharic