>

የነቁ ዜጎች የዘረኞች እና የአምባገነኖች ኢላማ ለምን ይሆናሉ (ሸንቁጥ አየለ)

የነቁ ዜጎች የዘረኞች እና የአምባገነኖች ኢላማ ለምን ይሆናሉ

ሸንቁጥ አየለ


* …ቲና በላይ በኢንጂነሪንግ የተመረቀች ወጣት ነች::ልዩ እና የነቃች ዜጋ በመሆኗም የወገኖቿ ሞትና ስደት የሚያንገበግባት ህሊናዋ የበለጸገ ዜጋ ነች::

የወገኖቿ ሞት እና ስደት የሚቆረቁራት ዜጋ ብቻ ሳትሆን ህዝቧ ተደራጅቶ እራሱን ያድን ዘንድ ሞራልም የምትሰጥ ነች::

—–

በጣት ከሚቆጠሩ የሴት ጀግኖች መሃከል የተገኘች እንደ እነ አስቴር  እና  እንደ እነ መስከረም አበራ ሁሉ የወገን መከራዉን በዝምታ ከማዬት የምትችለዉን ለማድረግ የፈቀደች ንቁ ዜጋ ነች::

—–

እንግዲህ ይህች የነቃች ዜጋ ወንጀሏ አንድ ብቻ ነዉ::የወገኖቿን ሞትና ስደት ጉዳዬ ነዉ የሚል ህሊና ላይ መድረሷ ነዉ::ዘረኞች እና አምባገነኖች በቲና በላይ ላይ Tina Belay በጋይንት ማጎሪያ ካምፕ  ብዙ መከራ እያደረሱባት ይገኛሉ::  የነቁ ዜጎች የዘረኞች እና የአምባገነኖች ኢላማ የሚሆኑት ያልነቃዉን ብዙሃን ህዝብ አፍኖ ለማጣፍት የሚሰራዉን ሀይል ወንጀሉን ስለሚያጋልጡበት ነዉ::

እንጂማ ቲና በላይ በራሷ የስራ ፈጠራ ዉጤት እራሷን የምታስተዳድር ብቻ ሳይሆን ለሀገርም የምታስብ ዜጋ ልትሸለም የሚገባት ወጣት ሆና ሳለ መታሰር እና መበሳቆል አልነበረም ሽልሟቷ::

Filed in: Amharic