>

የተረኝነት መጋለጥ የቦነነው ሜካፕ !! (አሳዬ ደርቤ/ሳሙኤል ሀይሉ)

የተረኝነት መጋለጥ የቦነነው ሜካፕ !!

አሳዬ ደርቤ/ሳሙኤል ሀይሉ

 *…. ምድር ላይ ካለው መራር እውነታ ጋር የማይጣመው የጠ/ሚሩ ዲስኩር…!!!

➔በትሕነግ እና በኦነግ የተፈጸሙ መከላከያ ሠራዊትን የመውጋት ወንጀል ለፋኖ ያከፋፈለ፤

➔የአማራ ሕዝብን ከመከላከያ ሠራዊቱና ከብሔር ብሔረሰቦች ጋር ያቃቃረ፤

➔ወራሪው ጦር ከመከላከያው ማርኮ የወሰዳቸውን ክላሾች ያስመለሰውን ፋኖ በመሳሪያ ነጣቂነት የወነጀለ፤

➔የኢትዮጵያን ሕዝብ ችግሮች ወደ ጎን ገፍቶ መንግሥታዊ ቅዠቶችን ያካተተ፤

➔በዓይን የሚታየውን ተረኝነት በሚኒስትር ሹመት ያስተባበለ፤

➔ጸረ አማራ ንግግሮችና አሽሙሮች የተንጸባረቁበት፤

➔በርካታ ዝባዝንኬዎች የተካተቱበት፤

➔በእራስ መተማመን የታጀቡ በርካታ ውሸቶች የተነገሩበት

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተረኝነት የሰጡት ከለላ ግን ሃገሪቷን በተገቢው የማያውቁ መሆናቸውን ነው …!!!

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተረኝነትን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው መልስ ለማምታታት በመሞከር ቀሽም መሆኑን በሚገባ አጋልጧል።

ሕዝቡ #ተረኝነት እያለ እየጮኸ ያለው ባለፉት ሦስት ዓመታት ኦሮምኛ ተናጋሪ የብልጽግና አባላት በየመስሪያ ቤቱ በብዛት እየተቀጠሩ ወይም እየተመደቡ መሆኑን እና በንግድ ጭምር ኦሮምኛ ተናጋሪ የብልጽግና አባላት በከፍተኛ ቁጥር እየጨመሩ መምጣታቸውን በተጨባጭ መመልከቱን ለመግለጽ ነው ።

እሱ ግን ከአጠቃላይ ቅጥር አንፃር አንሸዋርሮ መልስ መስጠተ የሚቀርብለትን ጥያቄ የማዳመጥ ችግር ያለበት ወይም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከፍተኛ ንቀት ያለው መሆኑን ነው የሚያመለክተው ።

ሕዝቡ በኦሮምኛ ቋንቋ “አከም” በማለት ሰላምታ መስጠት ጀምሯል ፣ ከዚያ ያለፈ ግን መናገር አይችልም በማለት እራሱ ጠቅላዩ ጭምር ሕዝቡ ገዢዎችን ለመለማመጥ ተገዶ ኦሮምኛ ለመናገር የሚያደርገውን ጥረት ለፓርላማው ገልጿል።  ሕዝቡ ባልተለመደ ሁኔታ “አከም” በማለት በኦሮምኛ መናገር የጀመረው እኮ በየመስሪያ ቤቱ የሚገኙት አገልግሎት ሰጪዎች በብዛት ኦሮምኛ ተናጋሪ የብልጽግና አባላት በመሆናቸው የተነሳ “አከም” ካልተባሉ ተገቢውን መስተንግዶ ስለማይሰጡት ነው።

ጠቅላዩ ለተረኝነት የሰጠው ከለላ ግን ሃገሪቷንም ህዝቡንም በተገቢው የማያውቃት መሆኑን ከማሳየት በቀር ሌላ ትርጉም የለውም።  እያንዳንዱ ምላሹ የመጨረሻ እንጭጭ መሆኑን የሚያጋልጥ ነበር። ”

———–

የህወሓት ዘመን መከላከያ በጀነራል ማዕረግ፣ በኮለኔል ማዕረግ፣ በሻለቃ፣  በዕዝ ፣ በብርጌድ … ስንት ፐርሰንቱን ትግሬ እንደተቆጣጠረው ሲዘረዝር ከርሞ አሁን ተረኛ ሆኖ በብሔር ሲያጨማልቀው የኔ ሲሆን የብሔር ፐርሰንት አውጥቶ ማጋለጥ ወንጀል ነው ብሎ እርፍ አለው።

ሲያቅለሸልሽህ ውሎ በአፍንጫህ ቢወጣ ዝም የሚል የለም።  ሜካፕህ ተራግፎ  ደምስርህ ግንባርህ ላይ ቢጋደምም ተረኝነትህን ማጋለጥ አንተውም።

Filed in: Amharic