>

በሃያ ሚሊዮኖች ደም የኦህዴድ ስልጣን ሲደላደል ...!!! (ሸንቁጥ አየለ)

በሃያ ሚሊዮኖች ደም የኦህዴድ ስልጣን ሲደላደል …!!!

ሸንቁጥ አየለ


* …. እለት በእለት በሚፈስ የእናቶች እምባ የጎበዞች ደም እየታጠበ ያለው ብልጽግና በውድቀቱ አፋፍ ላይ

———–

በህዉሃት እና በኦህደድ መካከል የተደረገዉ ጦርነት የአቢይ ስልጣን ማደላደሊያ ነዉ:: 11 ሚሊዮን አማራ ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ ወድቋል::4 ሚሊዮን አፋር ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ ወድቋል:: 4 ሚሊዮን ትግሬ ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ ወድቋል:: ዛሬ እነዚህን ሃያ ሚሊዮን ዜጎች ዞር ብሎ የሚያያቸዉ የለም::በርሃብ አለንጋ:በብርድ እና በበሽታ እየተጠበሱ ነዉ:: በጦርነቱ ያለቀዉን ህዝብ እግዚአብሄር ብቻ ያዉቀዋል::

አቢይ አህመድ በሃያ ሚሊዮን ህዝብ ደም ላይ የኦህዴድን ስልጣን አደላድሎ ወጥቷል:: ከሁሉም በላይ  በስኳድ የተጠረነፉ ገገማ ካድሬዎችን ከጎኑ አሰልፎ አማራን እየቀጠቀጠ ነዉ::

በሃያ ሚሊዮን ደም ኦህዴድ ስልጣኑን አደላድሎ ቁጭ አለ::ጦርነቱን ሲቃወሙ የነበሩትን ጋዜጠኞች እና ጸሃፊያንን ኦህዴድ እያሳደድ እያሰረ ነዉ::ይባስ ብሎም ለስልጣኑ መደላድል ይሆነዉ ዘንድ ከሱ ጋር ተባብረዉ ህዉሃትን የወጉ ፋኖዎችን  እያሳደደ እየገደለ እና በጅምላ እያሰረ ነዉ::እንደሚባለዉ ከአስር ሽህ በላይ ፋኖ” ልዩ ሀይል እና ከመከላከያ ዉስጥ ተመርጠዉ ጥርስ የተነከሰባቸዉ አማራዎች ታስረዋል::

ስኳድ ትርፋና ኪሳራዉን አስልቻለሁ ብሎ ቅየኦህደድ/ኦነግን የመጨረሻ ግብ ለማሳካት ከእኛ በላይ ካድሬ ምን ማሞጥሞጥ ነዉ ብሎ በሃያ ሚሊዮንህ ህዝብ ደም ላይ ከትከት ብሎ እየሳቀ ነዉ::

Filed in: Amharic