>

*... የጥላቻ ሕጉ እሳቸውን አይመለከትም እንዴ ....???  (ሳሙኤል ሀይሉ)

የጥላቻ የፍጅት ቅስቀሳ …!!!

ሳሙኤል ሀይሉ

*… የጥላቻ ሕጉ እሳቸውን አይመለከትም እንዴ ….??? 


ፎቶግራፉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ “አዲስ አበባ ውስጥ ከፍተኛ ኦሮሞ ጠል ሃይሎች ኦሮምኛ ተዘመረ አሉ” በማለት በተናገሩበት ቅጽበት የነበራቸውን ስሜት የሚያሳይ ነው ። የፊት ገጽታቸው በራሱ ብዙ የሚናገረው ነገር ቢኖርም ዋና ነጥብ ወዲህ ነው ።

አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በፓርላማ ስብሰባ ላይ ቀርቦ የአንድ አካባቢ ሕዝብ ለሌላ አካባቢ ሕዝብ ከፍተኛ ጥላቻ አለው ብለው መናገራቸው ሕዝብ ለሕዝብ እንዲጋጭ ጥሪ ከማድረግ እና ምናልባትም የዘር ፍጅት እንዲደረግ ከመቀስቀስ በምን ይለያል ?

አንድ የኢትዮጵያ ዜጋ የሌላን ክልል መዝሙር አልዘምርም በማለቱ በምን ሂሳብ ነው የማህበረሰብ ጥላቻ አለበት ተብሎ መደምደም የሚቻለው ? አዲስ አበባ በቻርተር የሚተዳደር የፌዴራል ከተማ እንደመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ የሚማሩ ተማሪዎች የከተማውን መዝሙር አልያም የሃገሪቱን ብሔራዊ መዝሙር ነው እንዲዘምሩ የሚጠበቅባቸው። ይህም ሆኖ ሙሉ ፈቃዳቸው መሆን አለበት። ኦሮሞ ክልል ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንኳን የአማራ ክልል መዝሙር ለመዘመር በአማርኛ ቋንቋ መናገር አደጋ የሚያስከትልበት ሁኔታ በሳቸው ዘመን መፈጠሩን እያወቁ ይህን መናገራቸው አስገራሚ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ሕዝብ ውስጥ ለኦሮሞ ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው አሉ በማለት የኦሮሞ ሕዝብ የአዲስ አበባን ሕዝብ እንዲጠላ ብሎም ለከፋ የበቀል እርምጃ እንዲዘጋጅ ወይም እርምጃ እንዲወስድ ቀስቅሰዋል ።

የአዲስ አበባ ሕዝብ የኦሮሞ ሕዝብ ላይ ቆሻሻ እየደፋ ነው በሚል የተናገሩ ሲሆን ፣ በዚህም በየትም ሀገር የሚኖሩ ተጎራባች ማህበረሰቦች ተደጋግፈው የሚኖሩበትን የማይካድ እውነታ ለግል የፖለቲካ አጀንዳ በሚመች መልኩ በመጠምዘዝ በህዝቦች መሐከል አለመተማመን እና ጥላቻ እንዲኖር የሚያደርግ ንግግር ተናግረዋል ።

ተራ የኦህዴድ ፅንፈኛ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች ሌላውን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለማሸማቀቅ በየዕለቱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያቀረሹትን ተመሳሳይ ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት መናገራቸው እጅግ አደገኛ ብቻ ሳይሆን የማህበራዊ ሚዲያው ተመሳሳይ ቅርሻት ምንጭ እሳቸው ይሆኑ እንዴ የሚያስብል ጭምር ነው ።

የጥላቻ ሕጉ እሳቸውን አይመለከትም እንዴ ? 

ንግግራቸውን ለመስማት 

https://fb.watch/dHuiAemgTj/

Filed in: Amharic