>

ካድሬ ዳኛ  ሆነው ህዝብ ሲበደሉ የነበሩ አሁን ሌቦች ሲባሉ ተነሱ....!!! (ግርማ ካሳ)

ካድሬ ዳኛ  ሆነው ህዝብ ሲበደሉ የነበሩ አሁን ሌቦች ሲባሉ ተነሱ….!!!

ግርማ ካሳ


*…. . ጠ/ሚሩ ዐቢይ በፓርላማ ዳኞቼ ሌቦች፣ ዐቃብያነ ሕጉም ሌቦች፣ ፖሊሶቼም ሌቦች ናቸው አሉ።

እናማ . . . በቃ ተክሳሾች ንጹሐን ናቸው ማለት ነዋ።

ሌባ ያስራል፣ ሌባ ይከስሳል፣ ሌባ ይፈርዳል።

በአማራ ክልል ያሉ ዳኞች ማህበር አብይ አህመድ በፓርላማ ዳኞችን በተመለከተ ለተናገረው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ “1ኛ ደረጃ ሌባ ዳኛ ነው”  ሲል በጅምላ ነበር ዳኞችን የከሰሰው፡፡

“ይህ ንግግራቸው ከፍርድ ቤት ተፈጥሯዊ ባህሪ አንጻር በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመኔታ የሚያሳጣ እኛ ገጽታን የሚያበላሽ፣ ንጹህና ምስጉን ዳኞች እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያሸማቅቅ እና ሞራላቸውን የሚነካ፣ የዉጭ ኢንቨስተሮችም ሆኑ ባለሃብቶች በሃገሪቱ የሚተማመኑበት የዳኝነት አካል መኖሩን አምነው መዋ ውለ ንዋያቸውን በልማት ላይ እንዳያፈሱ አሉታዊ ተጽኖ የሚፈጥር ነው”  ነው መግለጫው የሚለው፡፡

የጠቅላዩ ንግግር፣ ያለውን ሁኔታ ያላገናዘባ  ያልተገባ፣ እንደሆነ በመግለጽ  ዳኞች ጠቅላዩ የተናገረው ወደ ጎን በማድረግ ስራቸው እንዲሰሩ አሳስቧል፡፡ በሌላ አባባል ለዶር አብይ ንግግር ቦታ አትስጡ በሚል፡፡

የዳኞች ማህበር በዚህ መልኩ ድምጹን ማሰማቱ ጥሩ ነው፡፡ ሆኖም ዳኞች አሁን እነርሱ ሲሰደቡ ፣ የነርሱ ክብር ሲነካ ነው አሁን ለምን ያሉት፣  እነ አብይ አህመድ በውሸት ክስ ዜጎችን ሲከሱ፣ ሲያዋክቡ፣ ሲያስሩ .. ለዜጎች ሳይሆን ፣ ከአፋኙ መንግስት ጎን በመሆን ፣ ፖሊሶችና አቃቤ ሕጎች የሚፈለጉትና የሚጠይቁት ሁሉ እያደረጉ፣ እነርሱ ራሳቸው በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ግፍ ተባባሪ ነበሩ፡፡ አሁንም ናቸው፡፡

የዳኞች ክብር አሁን አብይ ሌባ ስላላቸው ሳይሆን በፊትም ለፍትህ የቆሙ ሳይሆን  አቃቤ ሕግ የሚፈልገውን የሚያፈጽሙ በመሆናቸው ሕዝብ በነርሱ ላይ አመኔታ ካጣ ቆይቷል፡፡ ፍርድ ቤቶች የገዢው አፋኝ ቡድን አካል ተደርገው መታየት ከጀመሩ ቆይቷል፡፡

ይህ መግለጫ አብዛኞቹ ዳኞች ጥሩዎች ናቸው፣ ሌቦቹ ጥቂት ቢኖሩም ነው የሚለው፡፡ እኔ ደግሞ አብዛኞቹ ካድሬ ዳኛዎች ናቸው፣ ሃቀኞች በጣም ጥቂት ናቸው ባይ ነኝ፡፡

Filed in: Amharic