>
5:13 pm - Friday April 18, 0966

በዝግመተ ለዉጥ ሂደት ዝንጀሮዎች እና በርካታ እንሰሳዎች የደረሱበት ደረጃ ላይ ያልደረሱ "ሰዎች" ...!!! (ሸንቁጥ አየለ)

በዝግመተ ለዉጥ ሂደት ዝንጀሮዎች እና በርካታ እንሰሳዎች የደረሱበት ደረጃ ላይ ያልደረሱ “ሰዎች” …!!!

ሸንቁጥ አየለ


–ከኦህዴድ/ኦነግ እና ከህዉሃት ዘረኞች ይልቅ የኢትዮጵያ ታላቅ ጠንቅ እና ጠላት የብአዴን ጎጠኞች ናቸዉ::ምክንያትስ ካላችሁ ደግሞ እንደሚከተለዉ ነዉ::

–የኦህዴድ/ኦነግ ዘረኞች ቢያንስ በጎሳ ህሳቤ ደረጃ ደርሰዋል::የህዉሃት ዘረኞችም ቢያንስ በጎሳቸዉ ደረጃ ደርሰዋል::እነዚህ ሁለት ዘረኛ ሀይሎች የሚያስቡት:የሚያልሙት እና ሁሉንም ነገር የሚተገብሩት በጎሳቸዉ ደረጃ ነዉ::ሰዉ በጎሳ ደረጃ ተወስኖ ከቀረ ገና እሰዉነት ደረጃ ላይ አልደረሰም::የሰዎች እኩልነት እና አብሮነት ፈጽሞ ሊገባዉ አይችልም::

–ዝንጀሮዎች እና በርካታ እንሰሳዎች የዬዝርያቸዉን ማንነት ስለሚያዉቁ ከዝርያቸዉ ጋር አብሮ መኖር ያዉቃሉ::የጎሳ ፖለቲካ የሚያራምዱ ዘረኞች ግን ከዝንጀሮዎች እና ከበርካታ እንሰሳት ደረጃ እንኳን አልደረሱም::እነዚህ ዘረኞች የሰዉልጆችን አብሮነት እና አኩልነት አይቀበሉም::የሰዉ ልጅ አንድ ነዉ ብለዉ ስለማይቀበሉ ገና በጎሳቸዉ ከረጢት ዉስጥ ታጥረዉ ነዉ ያሉት::

–ሆኖም ከጎሰኛ ዘረኞችም ያነሰ ደረጃ ላይ ያለ ዝግመተ ለዉጡ በዝንጀሮና በ እንሣት የተበለጠ ብቻ ሳይሆን ገና ዝግመተ ለዉጥ ዉስጥ ለመግባት እየተንገዳገደ ያለ ፍጥረትም አለ::ይሄም ሀይል ብአዴን ዉስጥ የተሰባሰበዉ የብአዴን ጎጠኛ ሀይል ነዉ::ይሄ ጎጠኛ ሀይል ገና እንደ ነገድ አስተሳሰብ  ደረጃ  ላይ   እንኳን ያልደረሰ  ሀይል ነዉ::

–የኦህዴድ/ኦነግ እና የህዉሃት ዘረኛ ሀይሎች ከብአዴን ጎጠኛ ሀይሎች በዝግመተ ለዉጥ ሂደት የተሻለ ደረጃ ላይ ናቸዉ::

–ሁላቸዉም ግን ገና ሰዉነት ደረጃ ላይ አልደረሱም::ሌላዉ ቀርቶ ከዝንጀሮ እና ከብዙ እንሰሳት በጅጉ ያነሱ ፍጥረታት በመሆናቸዉ ገና የሰዉ ዝርያ መሆናቸዉን አላወቁም::ዝንጀሮዎች እና በርካታ እንሰሳቶች ዝርያዎቻቸዉን ስለሚያዉቁ አብሮ በኩልነት ለመኖር ችግር የለባቸዉም::የኦህዴድ/ኦነግ እና የህዉሃት ዘረኛ ስብስብ እንዲሁም የብአዴን ጎጠኛ ሀይሎች ግን ገና ዝንጀሮዎች እና እንሰሳዎች የደረሱበት ዝግመተ ለዉጥ ላይ አልደረሱም::

–በዝግመተ ለዉጥ ሂደት ዝንጀሮዎች እና በርካታ እንሰሳዎች የደረሱበት ደረጃ ላይ ያልደረሱ “ሰዎች” የመጀመሪያ ስራቸዉ የጎሳ ፖለቲካን በመከተል ሰዎች አብረዉ ሊኖሩ የማይችሉ ዝርያዎች መሆናቸዉን መስበክ: ሰዎች አብረዉ እንዳይኖሩ ማባላት እና ማፋጀት ዋናዉ ግባቸዉ ነዉ::

–ከነዚህ የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ ዘረኞች በከፋ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘዉ ደግሞ ገና የጎሳ ፖለቲካ ደረጃ ላይ እንኳን ያልደረሰዉ የብአዴን ጎጠኛ ስብስብ ነዉ::ከጎሳ ከረጢትም ዉጭ ባለ የጎት ከረጢት የተጠረነፈ::የብአዴን ጎጠኛ ስብስብ ከራሱ ጎሳ ጋር እንኳን መኖር የማይችል በዝግመተ ለዉጥ እጅግ ዝቅተኛዉ ደረጃ ላይ የሚገኝ ስብስብ ነዉ::

መደምደሚያ

–በዝግመተ ለዉጥ ሂደት ዝንጀሮዎች የደረሱበት ደረጃ ላይ ያልደረሱ “ሰዎች” የመጀመሪያ ስራቸዉ የጎሳ ፖለቲካን በመከተል ሰዎች አብረዉ ሊኖሩ የማይችሉ ዝርያዎች መሆናቸዉን መስበክ:  አብረዉ እንዳይኖሩ ማባላት እና ማፋጀት ዋናዉ ግባቸዉ ነዉ::

-ከኦህዴድ/ኦነግ እና ከህዉሃት ዘረኞች ይልቅ የኢትዮጵያ ታላቅ ጠንቅ እና ጠላት የብአዴን ጎጠኞች ናቸዉ::ምክንያቱም ገና ሰዉነት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከጎጥ ወደ ጎሳ ከዚያም ወደ ሰዉነት ህሳቤ ለመድረስ የሽግግር ሂደቱ እጅግ አዝጋሚና ብዙ ሀይል የሚጨርስ ስለሆነ ነዉ::

Filed in: Amharic