በባህር ዳር የታፈኑት ከወር ቦኃላ ፍርድ ቤት ቀረቡ… !
አሻራ ሚዲያ
የአሻራ እና የንስር ጋዜጠኞች እና ትህትና በላይ(ቲና) የፍርድ ቤት ውሎ…!!!
ከሳሽ የፌዴራል ፖሊስ የመብት አቀንቃኝ ትህትና በላይ(ቲና) ፣ 3 የንሥር ብሮድካስት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 5 የአሻራ ሚዲያ ጋዜጠኞች ማለትም ቀለሙ ገላጋይን፣ ጋሻዬ ንጉሴን፣ ጌትነት ያለውን፣ሐብታሙ መለሰን እና ዳንኤል መስፍንን “መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት” በሚል ወንጅሏል። ለዚህም 14 የምርመራ ቀናትን ጠይቆ በአማራ መስተዳድር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተፈቅዶለታል።
በክርክሩ ሂደት፣ ወንጀሉ በመገናኛ ብዙሃን የተፈጀመ ከሆነ፣ በአዋጅ ቁጥር 1238/13 አንቀፅ 2 እና 86 መሰረት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሳይፈቀድ ቀጥታ ክስ መመስረት እንደሚገባ የህሊና እስረኞቹ ጠበቃ ገልፀው፣ እስረኞቹ ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ለፊታችን ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ጋዜጠኞቹ እና ትህትና በላይ ከባሕር ዳር በባለፈው ግን ቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. የታፈኑ ሲሆን፣ ዛሬ አንድ ወር ሞልቷቸዋል። በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረባቸው ቢሆንም፣ በህገ- ወጥ መንገድ ተወስደው ከነበሩበት ንፋስ መውጫ እስር ቤት ወደ ባሕር ዳር ተመልሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት ባለፈው ግንቦት ዘጠኝ ነው።
አሻራ ሚዲያ በግፍ እስር ላይ የሚገኙት አምስት የይዘት እና የካሜራ ጋዜጠኞቹ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል። ከጋዜጠኞች በተጨማሪ የአሻራ ሚዲያ መገልገያ ንብረቶችም በፖሊስ ተወስደዋል። ከተወሰዱት መካከል የቪዲዮ ካሜራዎች፣ መቅርጸ ድምፆች፣ ላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ይገኙበታል።
/