>
5:21 pm - Saturday July 21, 0288

ደራሲና ጋዜጠኛ አቤ ጉበኛ  (ታሪክን ወደኋላ)

ደራሲና ጋዜጠኛ አቤ ጉበኛ

ታሪክን ወደኋላ

ደራሲ አቤ በምዕራብ ጎጃም ዞን በአቸፈር ወረዳ በልዮ ስሙ ኮረንች አቦ በተባለ ቀበሌ ከአባቱ አቶ ጉበኛ አምባየነና ከእናቱ ወ/ሮ ይጋርዱ በላይ ሰኔ 25/1925 ዓ.ም ተወለደ።

ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ በመጀመሪያ የአብነት በይስማላ ደብረ ገነት ቅ/ጊ ቤ/ክርስቲያን ዜማውን ዳዊቱን ቅንኔውን ለ12 ዓመታት የተከታተለ ሊቅ ነው። አቤ በዘመናዊ ትምህርቱን በዳንግላ ከተማ ይከታተል የነበረ ሲሆን በ1946 ዓ.ም ዳንግላን ትቶ ወደ አ/አ በመሄድ  ባዕታ ቤ/ክርስቲያን ተጠግቶ እንደ ቆሎ ተማሪ ሆኖ ቆይተዋል።

አቤ ከልጅነቱ ጀምሮ ውስጡ የፁሑፍ ፍላጎት እና ችሎት ስለነበረው በ1949 ዓ.ም “ከመቅሰፍት ሰራዊት ይጠንቀቅ ሰውነት” በሚል ርዕስ አነስተኛ የግጥም መፅሐፍ አሳትሟል። አቤ በ26 ዓመቱ በማስታወቂያ ሚኒስቴር በጋዜጠኝነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በ1953 ዓ.ም ባሳተመው “የሮም አወዳደቅ” ስያሜ ያለው የተውኔት መፅሐፍ በወቅቱ ገበሬው በንጉሡ ስርአት ያለውን ብሶት እና ቁጭት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ፅሁፍ ነበር።

በ1955 ዓ.ም ባወጣው “የአመፅ ኑዛዜ” በተሰኘው ልብወለድ መፅሀፍ ተምረው ሆነ ሰርተው ሀብት ያገኙ  ሰዎች ድሀ ወገኖቻቸውን እንዲረዱ የሚያሳስብ ነበር።

በሐምሌ 1956  “ሰይፈ ነበልባል”የተሰኘው መፅሐፍ አሳትሟል ይህ መፅሐፍ ልክ እንደ “አልወለድም” መፅሐፍ ይታገዳል በሚል ጥርጣሬ ህዝቡ መፅሐፍን ለመግዛት ከፍተኛ ርብርብ ያደረገ ነበረ። በ 2 ወር ውሰጥ ብቻ  4 ጊዜ በተደጋጋሚ ታትሟል ይህ መፅሐፍ በደርግ ዘመን መንግስት ድረስ እስከ 1968 ዓ.ም የተሸጠ ሲሆን የሚመጣውን የደርግ መንግስት አገዛዝ ቀድሞ የተቸ መፅሐፍ ከመሆኑም አልፎ በኢትዮጵያ የስነፅሁፍ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው በ 2 ወር ውሰጥ ብቻ  4 ጊዜ በተደጋጋሚ ታትሟል ይህ መፅሐፍ በደርግ ዘመን መንግስት ድረስ እስከ 1968 ዓ.ም የተሸጠ ሲሆን የሚመጣውን የደርግ መንግስት አገዛዝ ቀድሞ የተቸ መፅሐፍ ከመሆኑም አልፎ በኢትዮጵያ የስነፅሁፍ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ሃያ አምስት (25,000) ሺህ ኮፒ ታትሞ የተሸጠ እና ከፍተኛ ስርጭት ያገኘ መፅሐፍ ነው።

አቤ የሚፅፋቸው መፅሐፍ ለመንግሥት አስቸጋሪ በመሆናቸው በ 1955 ዓ.ም አልወለድም በፃፈበት ወቅት በመንግስት ከፍተኛ ክትትል ይደረግበት ነበር።

አቤ ፖለቲካዊ ማህበራዊ ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን ለህዝቡ በፅሁፍ ያካሂደው የነበረው የብዕር ትግል ባለመርካቱ በተግባራዊ ለማድረግ በ 1957 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ በተካሄደው የህዝብ እንደራሴነት ምርጫ ለመወዳደር የ50 ሰዎች የድጋፍ ፊርማ ያገኘ ሲሆን ህዝቡ አቤ ለመምረጥ በነቂስ በወጣበት ጊዜ ዳሩ ግን የነፃነት ታጋዮ አቤ ሰኔ 21/1957 ዓ.ም በድንገት ሳይታሰብ በፀጥታ ሃይሎች ተወስዶ ታሰረ ብዙ እንግልትና ስቃይ ደረሰበት።

ብዙ ክትትል የሚደረግበት አቤ በቀን 3 ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ እየሄደ መፈረም በከተማው ውስጥ የሚዘዋወርባቸው ቦታዎችና ሰዓቶች ተወሰነበት ለጥበቃ ምቹ የሆነ ቤት አደረጉት በህዝብ መሰብሰቢያና መጠጥ ቤት እንዳይገባ ከአምደኞች፤ ከተጠርጣሪዎች እንዲሁም ከውጪ ሀገር ሰዎች እንዳይገናኝ ተደረገ ለቤተሰብ የሚፅፈው ደብዳቤ እንዲመረመር እና በወር ውስጥ ከ 50 ብር በላይ እንዳይዝ ተደረገ።….

አቤ ከ አራት ወር ተኩል በኃላ “ሞቻ የሰው ልጅ መሞቻ” ወደተባለው አስከፊው ቦታ ተወረወረ። እስከ 1961 ዓ.ም ለሶስት ዓመት ለእስራት ተዳረገ። በ 1969 ዓ.ም የፃፈው ፅሁፍ በታሰረባቸው 3 ዓመታት ያሳለፈውን ሁነታ አስፍሯል።

ቅዳሜ የካቲት 1/1972 ዓ.ም ቦታው ጎጃም በረንዳ ነው አቤ ጉበኛ ቀበሌ 34 አካባቢ  ተደብዶቦ ከአስፋልት ዳር ተዘርግቶ ወድቋል አቤ “አንሱኝ ተጠቃው ተጠቃው” እያለ ያቃስታል በወቅቱ በቦታው የደረሱ ሰዎች አንስተው ቀደም ብሎ አቤ ወደ ተከራየው አርባ ምንጭ ሆቴል ክፍል ወሰዱት በነጋታው እሁድ ጠዋት ፖሊሶች መጥተው ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ወሰዱት ሆስፒታል ከገባ ከግማሽ ሰዓት በኃላ ዶክተሮች አቤ መሞቱ አረጋገጡ።

የካቲት 4 በይስማ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የቀብር ስርአት ተፈፀመ። የሶስት ልጅ አባት የሆነው እና ከሃያ በላይ መፅሐፍት ለአንባቢ ያቀረበው የብዕር ታጋይ ደራሲ አቤ ጉበኛ ለሚወደው ሀገር እና ህዝብ በሙያው ሲታገል የነበረ የክፍለ ዘመኑ ጀግና ደራሲ ነው።

ክብር እና ዘላለማዊ እረፍት ለብዕረኛው አቤ ጉበኛ !!!

Filed in: Amharic