>

የተጠያቂነት ነገር፤ እነማን? (ያሬድ ሀይለማርያም)

የተጠያቂነት ነገር፤ እነማን?

ያሬድ ሀይለማርያም


በሀገር ደረጃ ገለልተኛ የፍትህ ተቋማት ቢኖሩን ኖሮ በአገራችን ውስጥ በተከታታይ ከተፈጸሙት አሰቃቂ የጅምላ ጭፍጨፋዎችና ከእርስ በርስ ጦርነቱ ጋር በተያያዘ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው እልቂት፣ ስቃይና እንግልት በቀጥታ ጭፍጨፋውን ከፈጸሙት አካላ በተጨማሪ የሚከተሉት ባለሥልጣናት ላይ ምርመራ ሊካሄድና ክስ ሊመሰረት ይገባ ነበር፤ ይገባልም።

1ኛ/ ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ የዜጎችን ግድያ ባለማስቆም እና አጥፊዎችን ባፋጣኝ ለፍርድ ማቅረብ ባለመቻል፣

2ኛ/ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ለተፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋዎች በዋነኝነት ሁሉም የህውሃት አመራሮች እና እንደየ ጉዳዩ አግባብ ደግሞ የፌደራል ባለሥልጣናት፣

3ኛ/ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ እና የክልሉ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች፤ በክልላቸው ውስጥ ማባሪያ በሌለው መልኩ በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲጨፈጨፉና ሲሰቃዩ እያዩ ድርጊቱን ባለማስቆም ወይም ማስቆም ባለመቻላቸው፣

4ኛ/ የአማራ ክልል ባለስልጣናት፤ በቅርቡ ከሥልጣን የወረዱትንም ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፤ በክልላቸው ውስጥ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ እና የዜጎች ስቃይ፣ ጭፍጨፋም በቸልታ በማየትና በማባባስ ጭምር፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በጅምላ ያለምንም የፍርድ ሂደት በማጎር፣

5ኛ/ የቤንሻንጉል ክልል ባለሥልጣናት፤ በክልሉ ውስጥ ላለፉት ሦስት አመታት በንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን ማስቆም ባለመቻል፤

በዋነኝነት ግን በሁሉም ክልሎች እነዚህን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊቶች የፈጸሙ አካላት ተጠያቂዎች መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ ከላይ በጠቀስኳቸው የመንግስት ሹሞች ላይ ግን ቀጥተኛ ምርመራና ክስም ሊመሰረትባቸው ይገባል።

ተጠያቂነት ከሌለ ፍትህ አይኖርም። ፍትህ ከሌለ ሰላም የለም። ሰላም ከሌለ ልማትና ብልጽግና ከንቱ ህልም ነው የሚሆኑት።

End Impunity!!

Filed in: Amharic