የአማራ ህዝብ እውነቱን ተቀበል !!
ሀብታሙ አያሌው
ማስታወሻህን ተመልከት ጥቅምት 22/2013 ዓ/ም ወለጋ ጉሊሶ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተፈፅሞ ፓርላማ ውስጥ መቆጣጠር አቅቷቸው በእንባ የተራጩ ነበሩ። “ጠቅላዩ ተገኝቶ ምላሽ ካልሰጠ በሌላ ማንኛውም ጉዳይ አንነጋገርም” በሚል ቁርጥ አቋም ተያዘ፤ መከላከያ ኦነግ ሸኔ አቅቶት ከሆነ ይነገረን ፣ ህዝባችን ታጥቆ ራሱን ይጠብቅ ተባለ…”
ማህበራዊ ሚዲያው ተናወጠ፣ አማራ ክልል ከፍ ያለ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ…”አብይ ኦነግ ነው፣ አራጃችን እራሱ ነው፣ ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይቅረብ” የሚሉ መፈክሮች ተሰሙ… ወዲያው …
ዐብይ አህመድ 5 ቢሊዮን ብር ባጀት ብሎ በካሽ በአንቶኖቭ ወደ ትግራይ ላከ፣ ከደብረጽዮን ጋር በስልክ መወያየቱም ተገለፀ። በማግስቱ የጉሊሶው የአማራ ጭፍጨፋ ፋይሉ ተዘግቶ የሰሜኑ ጦርነት ፈነዳ ተባለ… አራጅ እና ታራጅ በጋራ እንዝመት ተባለ … ሰሜን ወደመ።
አሁንም ተመልከት… ኦሮሚያ ወለጋ ጊምቢ ከ3ሺህ በላይ አማራ እንደ አውሬ ተጨፈጨፈ፣ በማግስቱ የብአዴን ዜና ህወሓት በቆቦ በኩል ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጀመረ የሚል ሆነ… አራጅ ፣ አሳራጅ ፣ ሽፋን ሰጪ የሚጫወቱብህ ለምን ይመስልሃል ?? የኔ ምላሽ አጭር ነው “ብአዴን በሚባል ትርፍ አንጀት” ስለምትመራ ነው። ቀዳሚ ትግልህን ከብአዴን ጋር አድርገህ እሱን ከመነገልክ ሌላው እዳው ገብስ ነው።
አከተመ።