>

በናዚ ኦነግና በዐቢይ አሕመድ ጥምር ጦር  ሙስሎሞች ሲፈጁ ኦነጋዊው ኡስታዝ ሁላ የት ገባ ..??? አቻምየለህ ታምሩ

በናዚ ኦነግና በዐቢይ አሕመድ ጥምር ጦር  ሙስሎሞች ሲፈጁ ኦነጋዊው ኡስታዝ ሁላ የት ገባ ..???

አቻምየለህ ታምሩ

“ጎንደር የእጇን ታገኛለት” እያለ ፋኖን ሲያወግና በየ መስጅዱ ሲሰለፍ የባጀው ኹሉ በወለጋ ምድር ያውም በመስጅድ ውስጥ ናዚው ኦነግ በግፍ ስላረዳቸው ከሶስት መቶ ኀምሳ በላይ የሚኾኑ ሙስሊሞች ጭፍጨፋ አልሰማም ይሆን?

ባለፈው ጎንደር ውስጥ ሙስሊምና ክርስቲያን አማሮች በተገደሉበት የንጹሐን ጥቃት ሙስሊም ብቻ የተጠቃ አድርጎ ከጣራው በላይ በማጮኽ ፋኖን ባልዋለበት ያላወገዘ ኡስታዝ፣ በአዲስ አበባ፣ ኦሮምያ በሚባለው ክልልና በሲልጤ ዞን ውስጥ የሚገኝ መስጂድ አልነበረም። ልብ በሉ! በጎንደሩ ጥቃት የተገደሉት ንጹሐን ሙስሊሞች ብቻ አልነበሩም፤ ገዳዩም ፋኖ አልነበረም፤ ሲጀመር አንድም ፋኖ በቦታው አልነበረም፤ ይኽንን ምስክርነት የሰጡም የዐይን እማኝ የኾኑ ራሳቸው የጎንደር ሙስሊሞች ናቸው። እንዴውም ጥቃቱን ያቀነባበሩት እነዚህ ወገኖች ናቸው!

በወለጋ ጊምቢ በመስጂድ ውስጥ ከሶስት መቶ በላይ ንጹሐን አማራ ሙስሎሞች በናዚ ኦነግና በዐቢይ አሕመድ ጥምር ጦር ሲጨፈጨፉ ግን የጎንደሩን ጥቃት ከጣራው በላይ በማስጮኽ  አማራን ያወገዘ ኦነጋዊ ኡስታዝ ሁሉ፣ በአዲስ አበባ፣ ኦሮምያ በሚባለው ክልልና በሲልጤ ዞን በሚገኙ መስጅዶች የሙስሊሞች ተቆርቋሪ ነኝ ብሎ  “ጎንደር የእጇን ታገኛለት” እያለ ሰልፍ የወጣው የአሕመዲን ጀበል ተከታይ ሁሉ በወለጋ ምድር በመስጅድ ውስጥ የተጠለሉ ከሶስት መቶ ኀምሳ በላይ አማራ ሙስሊሞች በኦነግና በዐቢይ አሕመድ ጥምር ጦር ሲጨፈጨፉ ድምጹ አይሰማም።

እነዚህ በአዲስ አበባ፣ ኦሮምያ በሚባለው ክልልና በሲልጤ ዞን ሰልፍ የወጡ አውጋዦች በወለጋ ምድር ያውም በመስጅድ ውስጥ ናዚ ኦነግና ዐቢይ አሕመድ ያካሄዱትን የሙስሉም አማሮች ጭፍጨፋ ጎንደር ሙስሊም ተጠቃ ብለው በየአደባባዩ እየወጡ ፋኖን ባልዋለበት እንዳወገዙት ኹሉ ናዚ ኦነግን በየአደባባዩ የማያወግዙት የአላማው ተጋሪዎችና የግብሩ አስፈጻሚዎች ስለኾኑ ነው።

መቼም ከአንገት በላይ በኾነ ድምጽት ግፉአኑ ጨፈጨፈ ብለው በስም የጠሩትን ናዚ ኦነግን ተጠያቂ ሳያደርጉ አላወገዙም እንዳይባሉ ብቻ በግብር ይውጣ አገላለጽ የወለጋውን የሙስሊም አማሮች ፍጅት የሙስሊም ጥቃት እንዳልኾነ ለማለባበስ የሞከሩን አንዳንዶችን በወለጋ ናዚ ኦነግና የዐቢይ አሕመድ ጥምር ጦር በሙስሊም አማሮች ላይ ያካኼዱትን ጥቃት እንዳወገዙ አድርጎ የሚቆጥር አይጠፋም አይባልም። ሆኖም ግን ጎንደር ውስጥ ባልዋለበት ፋኖን እንዳወገዙት ኹሉ ግን ግፉአን  ጨፈጨፈን ያሉትን ናዚ ኦነግን በስም ጠርተው ሙስሊሞችን በመስጅድ ውስጥ በጅምላ አረደ ብለው እስካላወገዙ ድረስ ከአንገት በላይ የግብር ይውጣ ነው!

Filed in: Amharic