>
5:14 pm - Sunday April 20, 1000

በሸኔ በማሳበቡ ግድያዎችና ማፈናቀሎች ጀርባ ሁሌም መንግስት አለ! መርማሪ ኮሚሽን ይቋቋም !! (አሳዬ ደርቤ)

በሸኔ በማሳበቡ ግድያዎችና ማፈናቀሎች ጀርባ ሁሌም መንግስት አለ! መርማሪ ኮሚሽን ይቋቋም‼️

አሳዬ ደርቤ 

እንደ ማሳያ ፩

*…. “ኦነግ ሸኔ የሚባለው ነፍሰ ገዳይ ቡድን በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያለ ነው። መንግሥት ነገሮችን ለማወሳሰብ ሲል እራሱ የፈጠረው ኃይል ነው። ለዚያም ነው በጠራራ ጸሐይ በከባድ መሳሪያ ንጹሐንን ገድሎ ሲሄድ ማንም የማይዘው!”

ኦቦ ቀጀላ ባንድ ወቅት ለአሐዱ ኤፍ ኤም ከተናገረው‼️

እንደ ማሳያ ፪

“በከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት የሆኑ 14 ሰዎች በኦነግ ሸኔ ተገደሉ” ተብሎ በመንግሥት ሚዲያዎችና አመራሮች የተገለጸው ውሸት ነው። ሰዎቹ የተገደሉት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ነው”

የኢሰመኮ ሪፖርት‼️

እንደ ማሳያ ፪

*…. ጭፍጨፋዉን የፈፀሙት ሽመልስ አብዲሳ “Gaachana Sirna” በሚል ስም ያደራጃቸው የኦሮሞ ሚሊሻዎች ናቸው !

የኦነግ ሸኔ  ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቤ

የጅምላ እልቂትን ማቃለል ሞትን እና ግድያን ማለማመድ:-

የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት ማስከበር የአንድ መንግሥት ትንሹ ግዴታ ቢሆንም ሥልጣን ላይ ያለው አካል ግን ላለፉት ሦስት ዓመታት ዜጎችን ከጥቃት ሊከላከል ቀርቶ የጅምላ እልቂትን በማቃለል ሞትን እና ግድያን የተለማመደ ሕዝብ በማፍራት ላይ ይገኛል፡፡

ከሁለት ቀን በፊትም በተፈጸመው ጭፍጨፋ የተገደሉ ንጹሐን ቁጥር ከሰባት መቶ በላይ መድረሱ ቢነገርም መንግሥት ተብየው አካል ግን የአገር ውስጥ ሚዲያዎችን አፍ አፍኖ የሟቾቹን ማንነትና ብዛት ከማድበስበሱም በላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ‹‹አሸባሪ›› ተብሎ የተፈረጀውንና ከዓመት እስከ ዓመት ዜጎችን የሚጨፈጭፈውን ነፍሰ ገዳይ ቡድን ‹‹ኢ-መደበኛ ኃይል›› በሚል መጠሪያ ጋርዶ ከደሙ ለማንጻት በመጣር ላይ ይገኛል፡፡

ይህ በመንግሥት መዋቅር የታገዘ ዘር ተኮር ጥቃትና አገራዊ ውድቀት ግን ከዚህ በላይ መቀጠል ስለሌለበት ገለልተኛ የሆኑ አገራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማትን ያካተተ መርማሪ ኮሚሽን ተቋቁሞ የሚከተሉት ነገሮችን እንዲያጣራ እጠይቃለሁ፡፡

1ኛ. ‹‹ኦነግ ሸኔ›› በሚል ባለቤት አልባ ሥም ሲጠራ ኖሮ ‹‹ኢመደበኛ ኃይል›› መባል የጀመረው ነፍሰ ገዳይ ቡድን ግልጽ በሆነ መልኩ ማንነቱ፣ ባለቤቱና ፍላጎቱ እንዲጣራ፣

2ኛ. በወለጋ እና በመተከል እንዲሁም በሁሉም ክልሎች እንደ አገር የተፈጸሙ ጥቃቶችን እና የወንጀሉ ተሳታፊዎችን የሚለይ ጥልቅ ምርመራ ተደርጎ ተሰውረው የቀሩና በድብቅ የተቀበሩ ዜጎች ብዛት በአኃዝ እንዲገለጽ፤ እንዲሁም በጥቃቱ ላይ የተሳተፉ አሸባሪዎች፣ ፖለቲከኞች እና የመንግሥት አመራሮች ተጠያቂ እንዲሆኑ፤

3ኛ. በተለያዩ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ተፈትሾ የወደቀውና የሆነን አካል ከማውደም ውጭ ማንንም በማይጠቅም ዘረኝነት ውስጥ ተሸጉጦ ያለ አንዳች የኃላፊነት መንፈስ አገራዊ እልቂት የሚፈጥሩ ንግግሮችን እና ተግባሮችን በማዛመት ላይ የሚገኘው የብልጽግና መንግሥት እንደ ሮዋንዳ ሳያጫርሰን እና እንደ ሶሪያ ሳያፈራርሰን በፊት በአገር ደረጃ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም እየጠየቅኩ ‹‹ጥያቄህ ጥያቄዬ ነው››› የምትሉ ወገኖች ሥሜ የተጠቀሰበት ስፍራ ላይ ሥማችሁን ተክታችሁ እንዲታጋሩት አሳስባለሁ፡፡

Filed in: Amharic