>

ንክኪ.....!!! (ሸንቁጥ አየለ)

ንክኪ…..!!!

ሸንቁጥ አየለ

 

የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ እና በማስጨፍጨፍ ሂደት ዉስጥ በሚከተሉት ሰዎች እና ድርጅቶች መሃከል ምን ልዩነት አለ?

1. ደመቀ መኮንን:-አማራን የሚጭፈጭፈዉን ስርዓት በም/ጠቃላይ ሚኒስቴርነት የሚመራ

2. ይልቃል ከፋለ:-አማራ እንዳይታጠቅ የሚቀጠቅጥ እና አማራን እጅና እግሩን አስሮ ለኦህዴ/ኦነግ  እርድ ያስረከበ

3. አገኘሁ ተሻገር:- ዐማራን በጎጥ የሚከፋፍል እና የአማራን ፋኖ የሚያሳድድ

4. አቢይ አህመድ_ የአማራ አራጅ ስራአትን በጠቅላይ ሚኒስቴርነት የሚመራ

5.ታገስ ጫፎ: _የአማራ አራጁ ስርዓት የፓርላማ አፈጉባኤ እና ስለ አማራ የጅምላ ፍጅት በፓርላማ እንዳይነሳ የሚከለክል

6.ኦነጋዉያን_ለሰባ አመታት አማራን በማረድ ላይና በመጨፍጨፍ ላይ የተሰማሩ

7.ህዋታዉያን_ዐማራ እንዲጨፈጨፍ አሁን ያለዉን ስርዓት ከነፍልስፍናዉ ያዘጋጁ እና አሁንም አማራ ሲጨፈጨፍ ከበሮ አንስተዉ የሚዘሉ

8.ኦህዴድ_የአማራን ህዝብ ኦሮሚያ ከሚባለዉ የተረት ተረት ክልል ጠርጎ ለማጥፋት በትጋት እየሰራ ያለ

9.ብአዴን_ትናት ከህዉሃት ጋር ዛሬ ከኦህዴድ ጋር ተባብሮ የአማራን ህዝብ በማስቸፍጨፍ ግንባር ቀደም የሜዳለያ ተሸላሚ

10.የአማራ ብሄረተኛ ተቃዋሚ ነን ብለዉ ሲያበቁ የአማራ ህዝብ ጭፍጨፋ ሲከናወን በዝምታ አፋቸዉን የለጎሙ:ከአለዉ አማራ አራጅ ስርዓት ጋር ተባብረ የሚሰሩ

11. እንደ ኢዜማ አይነት የኢትዮጵያዊነት የዜግነት ፖለቲካ እናራምዳለን ካሉ ብኋላ ኢትዮጵያ የተፈጠረችዉ በቅኝ ግዛት ነዉ::አንዱ ነገድ ለአንዱ አካባቢ መጤ ነዉ::መጤ የሆነዉን ነገድ ነዋሪ ነገዶች ጨፍጭፈዉ ቢያስመልሱ መሬታቸዉን ለማስመለስ የኢያደርጉት እንቅስቃሴ ስለሆነ መጤዎች ለምን ይጨፈጨፋሉ ብሎ መጮህ ልክ አይደለም የሚሉ

12.በዉጭ ሀገር ቁጭ ብለዉ ፋኖንን እነረዳለን ብለዉ ሲያበቁ እዉነተኛ ፋኖዎች መደምሰስ አለባቸዉ እያሉ የብአዴን ሚሊሻን ግን ፋኖ ነዉ እያሉ ከህዝብ በማጭበርበር የሚሰበስቡትን ገንዘብ ለብአዴን  ሚሊሻ የሚያዉሉ

13.በዉጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በየቀኑ እየተገኙ የብአዴን እና የብልጽግና እድሜ እንዴት እንደሚቀጥል ሲመክሩ እየባጁ መልሰዉ ደግሞ የህዝብ ተቆርቋሪና ተቃዋሚ በመሆን የአቢይን መንግስት የሚደግፉ

14.በለጠ ሞላ-የአብይ ሚኒስቴር እና ተላላኪ

እና ምን ለማለት ነዉ?

ዝም ብለህ አማራ አማራ አትበል ወይም ዝም ብለህ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያልክ አትጩህ ::የአማራን ህዝብ የሚያርዱት እና የሚያሳርዱት አማራ ያልሆኑት ወይም የሆኑት አይደሉም::የአማራን ህዝብ እያጠፋዉ ያለዉ ስርዓቱ ነዉ::

ማንም ከዚህ ስርዓት ጋር ንክኪ የሆነ ሁሉ የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የኢትዮጵያ ጠላት ነዉ::ደግሞ እንዴት የኢትዮጵያ ጠላት ይሆናል አትበል::ነገ ዛሬ የገደሉት መልሰዉ እንደሚገደሉ ብቻ ሳይሆን ለዘመዶቻቸዉም ሞትን እያተረፉላቸዉ መሆኑ እሙን ነዉና::

–እናም ዝም ብለህ ዝም ብለህ አማራ አማራ አትበል ወይም ዝም ብለህ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያልክ አትጩህ::አጥርተህ ተናገር::ሰዉ በኢትዮጵያዊነት ወይም በአማራነት እንደራጅ ስላለህ እንደ ቁም ነገር ወስደህ እንዘጥ እንተፍ አትበል::አጥርተህ አስተዉል::ሰዉ ምረጥ::

–የነገር ሁሉ መሰረቱ በአንድ ጥርት ባለ መሰረት ላይ ሊቆም የሚችል ሰዉ መገኘቱ ላይ ነዉ::

–ጥርት ያለ ራዕይ ግቡን የሚመታዉ ጥርት ያለ መሰረት ባላቸዉ ሰዎች መሰረት ላይ ሲቆም ነዉ::በተለይም መሰርቱ::

ቁልፍ ጭብጥ

ንክኪ ምናምንቴዎችን አበጥሮ በማዉጣት ማግለል የቻለ እና በታላቅ ሀገራዊ ራእይ በመመራት መላዉ ኢትዮጵያን ለማዳን ጨክኖ የሚነሳ የሰራዊት  ሀይል ብቻ ኢትዮጵያን ያድናታል፥፥ቁርጥ ያለዉ እዉነታም ኢትዮጵያን ጠቅልሎ ለማዳን የማይነሳ ሀይል ማንንም ማዳን አይችልም፥፥ በመከራ እግር ስር የወደቀችዉ ኢትዮጵያ ነች፥፥ ኢትዮጵያ በታላቅ ራእይ  በሚመራ ሰራዊት ሳትድን ማንም አይድንም፥፥

Filed in: Amharic