>
5:31 pm - Thursday November 12, 6409

የወለጋውን ጭፍጨፋ ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የአ/አ ዮኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊስ ተደበደቡ!! (ባልደራስ)

 በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል!!

 የወለጋውን ጭፍጨፋ ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የአ/አ ዮኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊስ ተደበደቡ!!

ባልደራስ

*… የአ/አ ዩኒቨርስቲ አማራ ተማሪዎች ከየዶርማቸው እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው!

በዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞው ቀጥሏል!!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፤ የዘር ፍጅቱን በመቃወም ሰልፍ እድርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አማራ ተማሪዎች እየታሰሩ ናቸው።

ተማሪዎቹ ዛሬ ለተጨፈጨፉት ድምፃቸውን ለማሰማት ባደረጉት ጥረት ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል።

አሁን ደግሞ፣ አማራ ተማሪዎች እየተለዩ እየታሰሩና እየታደኑ ይገኛሉ።

የወለጋውን የዘር ማጥፋት ለመቃዎም የወጡ የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊስ ተደበደቡ!!

ተማሪዎቹ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን በማቅረብ ላይ ሳሉ ነበር የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ድብደባ የፈፀሙት።

“የአማራ የዘር ማጥፋት ይቁም፤በማንነታችን መገደል ይብቃ፣ንፁሃን እየሞቱ መማር አልቻልንም፣ስርዓቱ በቃን”እና የመሳሰሉ መፈክሮችን በመያዝ ነበር ተማሪዎቹ ድምፃቸውን ያሰሙት።

ይሁን እንጅ፣ የዘር ማጥፈፉትን “መቃዎም አትችሉም”በሚል የመንግስት ታጣቂዎች በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል።

በህክምና ላይ የሚገኙ ተማሪዎች እንዳሉ ለማዎቅ ተችሏል።

Filed in: Amharic