“አማራን መጨፍጨፍ ሕገ ወጥ ድርጊት አይደለም”
የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ
አቻምየለህ ታምሩ
የናዚ ኦነግና የበላዔ ሰብዕ ዐቢይ አሕመድ ንጹሐንን ጨፍጨፊ ኃይል በወለጋ ጊምቢ ምድር በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ገበሬዎችን በአንድ ጀንበር በፈጀበት ማግስት የተጨፈጨፉት ግፉዓን አስከሬን ከየተጣለበት እየተሰበሰበ ተቀብሮ ሳያልቅ ከታች ሲነገር የምትሰሙት ፍጥረት ብአዴን የሚባለው ዘግናኝ ፍጥረት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኾነው ግርማ የሺጥላ ነው በቪዲዮ የምትሰሙትን ቃለ መጠይቅ አድርጓል።
ግርማ የሺጥላ በፋና ቴሌቭዥንበትናንትናው እለት በሰጠው ቃለ መጠይቅ “በአገሪቱ” ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች የሚፈጽሙትን ሕገወጥ ድርጊቶችን ከመቀነስ አልፎ ማስቆም ደረጃ የደረሰ ከፍተኛ እርምጃ በብል[ጽ]ግና ፓርቲ እንደተወሰደ ነግሮናል። ይህ የግርማ የሺጥላ ንግግር ተገልብጦ ሲታይ አማራን መጨፍጨፍ ሕገወጥ ተግባር አይደለም የሚል ይኾናል።
ለግርማ የሺጥላ አማራን መጨፍጨፍ ሕገወጥ መስሎ ቢታየው ኖሮ በወለጋ ምድር በሺዎች የሚቆጠር አማሮች በአንድ ጀንበር ባለቁበት ማግስት ተቀብረው ሳያልቁ የሽብር ቡድኖች የሚፈጽሙትን ሕገወጥ ድርጊቶችን ከመቀነስ አልፎ ማስቆም ደረጃ የደረሰ ከፍተኛ እርምጃ እንደተወሰደ ሊነግረን አይቃጣውም ነበር።
ምስኪኑ የአማራ ገበሬ ግን ላቡን እያንጠፈጠፈ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም እየከፈለ፤ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ሰጥቶ አዘባንኖ እያኖራቸው ያለው እንደዚህ አይነቶቹን አማራን መግደል ሕገወጥ ተግባር እንዳልኾነ በአደባባይ የሚናገሩትን ቅጥረኛ ነፍሰ በላዎች ነው።