>

በኦሮሞ ወረራ ስማቸው የተቀየረ ቦታዎች! (ጌጥዬ ያለው)

በኦሮሞ ወረራ ስማቸው የተቀየረ ቦታዎች!

ጌጥዬ ያለው
እየተደረገ ያለው ዘር የማጥፋት ርምጃ ነው!
አራት ኪሎ የከተመው የኦሮሙማ ስብስብ የራሱ ታሪክ እንደ ቅል መራራ የሚያንገሸግሸው የሌሎችን ደግሞ የሚናፍቅ ብሎም ለመስረቅ የሚጣጣር ቡድን ነው። ለመስረቅ ካልተቻለውም ለመፋቅ ይሞክራል። ይህ ስሁት አስተሳሰብ ከጥቂት ኦሮሞዎች አዕምሮ የሚመነጭ አይደለም።
ይልቁንም ከፖለቲካዊው የገዳ ማሕበር የሚጨለፍ ነው። የገዳ መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ ወረራ ነው። የገዳ መሪ ማለትም ‘ሉባ’ ለመሆን የመጀመሪያው መሪ ያልወረራቸውን ነገዶች መውረርና ማጥፋት ግዴታ ነው። ታዲያ በዚህ ሂደት በ16ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ኦሮሞዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በርካታ አካባቢዎችን ወረዋል። በስም የሚታወቁ ነባር የኢትዮጵያ ነገዶችን አጥፍተዋል። ዛሬ በመፅሐፍት የምናነበው ታሪክ የሌላ ሀገር ታሪክ እስኪመስለን ድረስ የቦታ ስሞችን በወረራ ቀይረዋል።
ለአብነትም የዛሬው ምስራቅ ወለጋ ነባር ስሙ ዳሞት ነበር። ከኦሮሞ ወረራ በፊት አማሮች ይኖሩበት ነበር። ከዚህ የገዳ ጭፍጨፋ አምልጠው በወቅቱ የሸሹ አማሮች ጎጃም ውስጥ መኖር ጀመሩ። ይህ መኖሪያቸው ዛሬም ድረስ ዳሞት እየተባለ ይጠራል። በተመሳሳይ የዛሬው ቄለም ወለጋ ቢዛሞ ይባል ነበር። የዛሬው ጅማ ገሙ፣ ጅባትና ሜጫ ገንዝ፣ ሰላሌ ግራርያ፣ ኢሉባቡር እናርያ፣ አሩሲ ፈጠጋር፣ ሐረርጌ ደዋሮ፣ ሞጆ ሽንብራ ኩሬ፣ ቦረና ወለቃ ይባሉ ነበር። ይህ የኦሮሞ ወረራ በመጨረሻም ተወግቶ ተመለሰ እንጂ የዛሬው የአማራ መስተዳድር ድረስ ዘልቆ አንጎት ይባል የነበረውን ራያ፣ ላኮመልዛ (ቤተ አማራ) ይባል የነበረውን ወሎ እስከማለት ደርሷል።
ይህንን ሁሉ ወረራ ሲፈፅም ከ28 በላይ ነባር የኢትዮጵያ ብሔሮችን ከምድረ ገፅ አጥፍቷል። ይህንን ሁሉ ያደረገው በራሱ የውጊያ ችሎታ አልነበረም፣ በቱርኮች ይታገዝ በነበረው የግራኝ አሕመድ ወረራ በተዳከመ ሕዝብ ላይ ጦር ስላነሳ እንጂ፤
በገዳ ማሕበር እየተመራ ይህንን ወረራ በሚያደርግበት ጊዜ ዛሬ ‘ኦሮሞ’ እየተባለ የሚጠራው ማሕበረሰብ መጠሪያ ‘ጋላ’ ነበር። ሆኖም በ1960ዎቹ የተማሪ ፖለቲከኞች የብሔር ንቅናቄን ሲጀምሩ አንድ ነገር አስፈራው። በጋላ ወረራ እና ጅምላ ጭፍጨፋ የጠፉ ነገዶች ጉዳይ አሳሰበው። በዚህ ወቅት በጅምላ ጭፍጨፋ ወንጀል እንዳይጠየቅ በመስጋት ስሙን ከጋላ ወደ ኦሮሞ ቀየረ። የጋላ ነፃነት ግንባር ይባል የነበረው ድርጅትም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ተባለ። ያለፈ ታሪኩን እየሸሸገ ዛሬም ሌላ ጅምላ ጭፍጨፋ በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ነው። ይሄኛው ስሙንም ነገ ሊቀይር ይችላል። እንዴውም ከአሁኑ ዳር ዳር ማለት ጀምሯል። ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔሮችን በገበሮነት ጠቅልሎ ኩሽ የሚባል ምናባዊ የጋራ ማንነት ለመፍጠር እየሞከረ ነው። ይህ የጥንት ግብፃውያንና ሱዳናውያን ስልጣኔን የኦሮሞ አድርጎ የማቅረብ ሙከራ ነው፤ መዳረሻውም ጥንታዊ አፍሪካውያን ነን ለማለትም ነው።
የሆነው ሆኖ ኦሮሙማ ታሪኩን የሚጠላው በሌብነት ስሙ ስለሚንቀሳቀስ ነው። የሌሎችን ታሪክ ለማጥፋት መባተሉም ከገዳ የወረራ እሳቤ የተቀዳ ነው። በሌሎች ታሪክ መጎምጀቱና የራሱ ለማድረግ መፍጨርጨሩ ደግሞ ከዚያው ከገዳ ማሕበር ውስጥ ከገበሮነት እሳቤ የተወረሰ ነው። ለዚህም በርካታ መገለጫዎች አሉት። ሰሞኑን በአማራ ላይ እየተደረገ ያለው ወረራም ከዚህ አስተሳሰቡ የሚመነጭ ነው። በለስ ቀንቶት አማራን ቢያሸንፍ ወደሌሎች ብሔሮችን ይዞራል።
Filed in: Amharic