>
5:13 pm - Monday April 18, 9267

ስንታየሁ ቸኮል በ30 ሺህ ብር ዋስትና ቢወጣም የፌደራል ፖሊሶች አግተውታል...!! (ባልደራስ)

ስንታየሁ ቸኮል በ30 ሺህ ብር ዋስትና ቢወጣም የፌደራል ፖሊሶች አግተውታል…!!!

 

ስንታየሁ ቸኮልን   ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ልብስ የለበሱ ፖሊሶች በፓትሮል  ሆነው፣ ባህርዳር ሳባታሚት ማረሚያ በር ላይ በመጠበቅ እገታ ፈፅመውበታል።

ማረሚያ ቤቱ በር ላይ ያገቱት የፌደራል ፖሊሶች ለምን እንደሚያግቱት ወዴትስ እንደሚወስዱት እንደ ህጋዉ ሰው ከማነጋገር ይልቅ ሀይል መጠቀምን ነበር የመረጡት።

ከበባ ከፈፀሙበት በኋላ ወደ ፓትሮል መኪናቸው ለማስገባት ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ፈጥረዋል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ወደ ፓትሮሉ እንዲገባ ሲጠይቁት፣ ማንነታቸውን እንዲያስረዱት ቢጠይቅ ምላሽ ሳያገኝ ከበው ሲያንገላቱት ታይቷል።

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Filed in: Amharic