>

ጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱ በድጋሜ በዋስ እንዲፈቱ ተወስኗል!!! (ሮሀ ሚድያ)

ጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱ በድጋሜ በዋስ እንዲፈቱ ተወስኗል!!!

ሮሀ ሚድያ


ከግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ የነበሩት ጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱb የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ የጠየቀውና የተፈቀለት የ15  ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውድቅ በማድረግ የ10 ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው እንዲወጡ ውሳኔ ሰቶ ነበር። የአቶ ታዲዮስ ባለቤት የጠየቀውን ብር በመክፈል የመፍቻ ትዕዛዝ ቢያቀርቡም ፖሊስ ውሳኔውን አልፈፅምም በማለት እስካሁን ድረስ በእስር ላይ ናቸው።

በተመሳሳይ ፍትህ ሚንስቴር በአቶ ታዲዮስ ላይ ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም “በፌደራል እና በክልል ህገ መንግስት የተቋቋመውን እንዲፈርስ ለማድረግ፣ አንዱ ወገን በሌላው ላይ የጦር መሳሪያ እንዲያነሳ ማነሳሳት፣በአንድ በተወሰነ ቡድን ማንነት ላይ ያነጣጣረ ጥላቻን ማነሳሳት፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከስነ ስርዓት ውጭ እንዲሆኑ ወይም እንዳይታዘዙ ማነሳሳት፣ የሃገሪቱን መንግስት ስም ማጥፋትና ማዋረድ” የሚሉ አምስት ክሶች መስርቷል።

አቶ ታዲዮስ ታንቱ የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚከለክል ስላልሆነ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ክሳቸውን በውጭ ሆነው እንዲከላከሉ እንዲወሰንልን ያቀረብነውን ጥያቄ ዓቃቢ ህግ “ክሱ ተደራራቢ ስለሆነ፣ አንደኛው ክስ ለብቻው የእድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ስለሆነ፣ ከወንጀሉ ክብደት የተነሳ በዋስ ቢሆኑ ችሎቱን አክብረው ሊቀርቡ ስለማይችሉና ድጋሜ ወንጀሉን ስለሚፈፅሙ” በማለት ተቃውሞ የነበረ ቢሆንም ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት በ15  ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ በአብላጫ ድምፅ ብይን መሰጠቱን ጠበቃቸው አቶ አዲሱ ጌታነህ ገልፀዋል ።

Filed in: Amharic