>

ይድረስ ለአፍኖ ሰዋሪዎች...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ይድረስ ለአፍኖ ሰዋሪዎች…!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

በተደጋጋሚ ሰዎችን ስልታዊ በሆነ መልኩ እያፈኑ መሰወር በአለም አቀፍ ሕግ ደረጃ በሰዎች ስብዕና ላይ የሚፈጸም ወንጀል – crime against humanity ተደርጎ እንደሚቆጠር አፋኞቹ ታውቁ ይሆን?

አፍኖ መሰወርን ለመከላከል ሲባል በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ጸድቆ በወጣው ድንጋጌ፤ Declaration on the Protection of all Persons from Enforced Disappearance, Adopted, 18 December 1992, በመግቢው ላይ ይሄን ይላል፤

“… enforced disappearance undermines the deepest values of any society committed to respect for the rule of law, human rights and fundamental freedoms, and that the systematic practice of such acts is of the nature of a crime against humanity.”

ግርድፍ ትርጉም፤ ሰዎችን ከፍቃዳቸው ውጭ አስገድዶ በማሰር መሰወር ወይማ ያሉበት ቦታ እንዳይታወቅ ማድረግ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ለሕግ የበላይነት፣ ለሰብአዊ መብቶች እና መሠረታዊ ነጻነቶች መከበር በቂ ትኩረት እንዳያገኙ ከማድረጉም በላይ ይህ አይነቱ የተደጋገመ እርምጃ በሰዎች ስብዕና ላይ ተነጣጥሮ እንደሚፈጸም ወንጀል –  crime against humanity የሚቆጠር መሆኑን ያሳስባል።

በቅርብ ጊዜ በጋዜጠኞች፣ በመብት ተሟጋቾች፣ ፖለቲከኞች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ላይ በመንግስት የጸጥታ አካላት እየተፈጸሙ ያሉ አፍኖ የመሰወር ተግባራት የአለም አቀፍ ሕግን የጣሰ እና እንደ crime against humanity ሊቆጠር የሚችል የወንጀል አይነት መሆኑን አፋኞቹ ሊያውቁት ይገባል።

Filed in: Amharic