>

የባሕር ዳርን ፋኖ ማፈን እና ማሳደዱ ቀጥሏል!! (የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር)

የባሕር ዳርን ፋኖ ማፈን እና ማሳደዱ ቀጥሏል!!

የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር


ባለፈው ሳምንት አፋኙና አሳዳጁ መንግሥት የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር አመራሮችን እና አባላትን አስሯል፤ ሌሎችን ለማሰረም በማሳደድ ላይ ይገኛል።

ይህ አፋኝ የሆነ መንግሥት በጣም አሳዛኝ እና አስነዋሪ ተግባር በአንድ ጓዳችን ቤተሰብ ላይ ፈፅሟል። ነገሩ እንዲህ ነው፦

ያው እንደተለመደው አፍኖ ለማሰር ወደ አንድ የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር ጓድ ቤት አፋኙ ግብረ -ሀይል ይሄዳል። ነገር ግን ጓዱ በቤቱ አልበረም። “የት ሄዶ ነው?”*በማለት ባለቤቱን ከልጆቹ ፊት እያንገራገሩና እያሰፈራሩ ያናግሯታል።

የባለቤቱም ምላሽ “እኔ አላወቅኩም። ለሥራ እንደ ወጣ ነው” የሚል ነበር። “በድጋሜ ስንመጣ ባይገኝ! ዋ!” በማለት ዝተውባት ይሄዳሉ።

በሚቀጥለው ቀን ወደ ቤቱ የሄዱት ከሌሊቱ 10:00 ሰዐት ነው፤ በውድቅት ሌሊት የአራት አመት ሕፃን ልጇን ጨምሮ ከሌሎች ልጆቿ ጋር በተኛችበት ቤቱን አስከፍተው “የት አለ ባለቤትሽ?” እያሉ ዛቱባት !?

ስልክ እንድትደውል አስገደዷት፥ ደወለች። ጓዳችንም ለሥራ በሄደበት  ስልኩን አንስቶ “ምንድን ነው? ሰላም ነው?” እያለ በማናገር ላይ እያለ በመሃል ግን የሚሰማው የአፋኞችን የዛቻ ንግግር ነበር፤ ‘እንዲህ በዪው’ እያሉ በቁጣ ድምፅ ሲጮሁባት ይሰማ ነበር። “ልጅህ ታሟል በአስቸኳይ ና በዪው” ይሏታል።

ተመልከት ወገን ሕፃናትን እንደ መያዣ ለመጠቀም የሚደረገው አስነዋሪና አሳፋሪ ተግባር በዚህ መልከልኩም ነው። ተመልከት ወገኔ በጨቅላ ሕፃናት ምንም በማያውቁት ፣በማይገባቸው እና አባታቸው ለአማራ ህዝብ ብሎ፤ ወገን ተደፈረ ብሎ ግንባሩን ለጥይት ፤ደረቱን ለጦር ሰጥቶ ጋሸና የዘመተን ጓድ ቤተሰብ እንደዚህ ማንገራገር።

አፋኞች ሆይ አንድ የዘናጋችሁት ነገር፤ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላትም  ሆነ መላው የአማራ ፋኖ  ውርደትን ለልጆቻችን አናወርስም፤ እኛ ሞተን ነፃነትን ለልጆቻችን እናጎናፅፋለን ብለን ነው ከጠላት ጋር የተፋለምነው፤ ለወደ ፊትም የምንፋለመው ለዚሁ ነው። በእኛ መስዕዋትነት ልጆቻችንን ነፃነት ይጎናፀፋሉ።

የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ድል ነው‼️

Filed in: Amharic