ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ከእስር እንዲፈታ ወይም የማይፈታበትን ምክንያት ካለ ችሎት ቀርቦ እንዲያስረዳ ታዞ የነበረው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ ሽብር ችሎት ቀርቦ፣ የዋስትናው ብይን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የታገደ ስለሆነ ሊፈፅም ያለመቻሉን አስረድቷል።
ችሎቱም ያልተፈታበትን ይሄን የጠቅላይ ፍ/ቤት ምክንያት ተቀብሎ አሰናብቶናል።
በዚህ መሠረት ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ዋስትና ሊፈታ አይገባም ክርክር ላይ ይግባኙን ለማድመጥ ለሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ቀጠሮ የያዘ መሆኑ ታውቋል።