>

 የባልደራስ ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ!! (ባልደራስ)

 የባልደራስ ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ!!

ባልደራስ


በሀገረ–አሜሪካ ለሁለት ወራት ቆይታ ያደረጉት የባለደራስ ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ፣ ዛሬ፣ ሐምሌ 6 2014 ወደ ኢትዮጰያ ተመልሰዋል።

ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ሲደርሱ የድርጅቱ አመራር አባላት አቶ ነብዩ ውብሸት እና ቀለብ ስዩም(አስቴር) ተቀብለዋቸዋል።

በአሜሪካ የነበራቸው ቆይታ በእጅጉ ሰኬት እንደነበር የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ነገ ሐምሌ 7 2014 ሥራ እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።

“እንደ ሀገርም፣ እንደ ድርጅትም ብዙ ስራ አለብን። የምናጠፋው ግዜ የለም”ብለዋል።

Filed in: Amharic