>

ዘገምተኛው ብአዴንና ከካርታ ላይ ሊፋቅ የተሴረበት  የአማራ ክልል … !?! (አሳዬ ደርቤ)

ዘገምተኛው ብአዴንና ከካርታ ላይ ሊፋቅ የተሴረበት  የአማራ ክልል … !?!

አሳዬ ደርቤ


*… ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በትሕነግ ተረቅቆ፣ በብልጽግና ጸድቆ ፣ በአንዴን  ተቋራጭነት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋገራል .  …!?!

➔የሚገርመኝ እኮ 12 ሺህ ፋኖ መታሰሩ አይደለም፡፡

በአማራ ክልል ውስጥ ሆነው አማራን የሚታገሉ ኦነጎች፣ ሸንጎዎች፣ ኮሚቴዎች… በብልጽግና እገዛ አቅማቸውን አጠናክረው ሲወጡ መመልከቴ እንጂ…

➔የሚያናድደኝ እኮ… የወልቃይት ማንነት በብአዴን አማካኝነት ለገበያ መቅረቡን መረዳቴ አይደለም፡፡

መላው አማራ ለወልቃይት ሕዝብ በጀት የሚለቀቅበትን፣ በወለጋ የሚኖሩ ወገኖቹ ደግሞ እረፍት የሚያገኙበትን ቀን ሲጠብቅ… የደቡብ ወሎን ዞን ለሁለት የሚሰነጥቅ…. ሰቆጣን ከአማራ ጉያ የሚነጥቅ…. አዊን- ከጎጃም፣ ጭልጋን- ከጎንደር የሚያራርቅ…. ሸዋን ከፊንፊኔ ጋር የሚሰለቅጥ…. እንደ አጠቃላይም የአማራ ክልልን ከካርታ ላይ የሚፍቅ… ግዙፍ ፕሮጀክት በትሕነግ ተረቅቆ፣ በብልጽግና ጸድቆ፣ በብአዴን ተቋራጭነት ወደ ተግባር ምዕራፍ መሸጋገሩ እንጂ….

ይሄን የረዥም ጊዜ ፕሮጀክት ታዲያ በቀላሉ ማክሸፍ የሚቻል ቢሆንም፣ ከእያንዳንዱ መፍትሔ ስር ብአዴን የተባለው የጎጥ ኮንትራክተር ‹‹ችግር›› ሆኖ ስለሚከሰት ብዙ ማውራቱ እርባና የለውም፡፡

Filed in: Amharic