>

ጭካኔን፣ ድንቁርናንና፣ ጥላቻን ከበታችነት ስነልቡና ጋር አስተባብሮ ያየዘው አራጁ ቡድን...!!! (መስቀሉ አየለ)

ጭካኔን፣ ድንቁርናንና፣ ጥላቻን ከበታችነት ስነልቡና ጋር አስተባብሮ ያየዘው አራጁ ቡድን…!!!

መስቀሉ አየለ

ባንድ ወቅት ለየኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የቀረበላቸው አንድ ጥያቄ ነበር፤

“አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከነገሩ ሁሉ የሚያስፈራዎት ነገር ምንድን ነው…?!” የሚል፤

ሲመልሱም፤ “እኔን የሚያስፈራኝና ክፉኛ የሚያሳስበኝ ነገር ቢኖር አንድ ያልተማረ ወጠጤ ደንቆሮ ከጠመንጃ ጋር የሚፈጽመው ያልተገራ ጋብቻ ነው። ለምን ቢባል ደደብ ሰው ሲባል ጠመንጃ መሸከም የሚያስክትለውን የህግና የሞራል ግዴታ የሚመዝንበት እውቀትና ሰብእና ስለማይኖረው ነው” ብለው ነበር። ፕሮፌሰሩ በግዜው  ይህንን የተናገሩት ስለ ሰው በላው አጋዚ እንደነበር አንድና ሁለት የለውም።

ዛሬም ደግሞ  በሌላኛው የአገሪቱ ክፍል ያ ጠመንጃ፤

በየመንደሩ እየዞረ ህጻናትና አረጋውያንን መግደልን እንደ ጽድቅ ስራ የተቀበለ፤ ጭካኔ ጀግንነት የሚመስለው ነገር ግን ከወንዶቹ መንደር ድርሽ የማይል፣

ጭካኔን ከድንቁርና፣

ድንቁርናን ከጥላቻ፣

ጥላቻን ከበታችነት ስነልቡና፣ የበታችነት ስነልቡናን ከተረኝነት ስሜትና የተረኝነትን ስሜት ደግሞ ከሃይማኖት ጽንፈኝት ጋር ደርቦ ሲመጣ የደርግን ውድቀት ተከትሎ መለስ ዜናዊ የተባለ እርጉም በምእራባውን የፖለቲካ አታሸዎች እየተደገፈ በብሄር ፖለቲካ ሽፋን የዘራውን የዘር ፖለቲካን ተግቶ ያደገውን የቄሮ ትውልድ ሳይረፍድ ባግባቡ ካልታረመና አበጀህ ካልተባለ በቀጣዮቹ አመታት ምን ያህል የማህበረሰቡ ክፉ ደዌ ሆኖ እንደሚቀጥል ጥርጥር የለውም።

መንጋው የዳቦ ስሙ በራካታ ቢሆንም

፩ ጃዋር ቄሮ ይለዋል፤

፪ ለማ መገርሳ የኦሮሞ ኢንስፕሬሽን ይለዋል፤

፫ የመንግስት ሚዲያ ሸኔ ይለዋል፤

፬ ጀነራል ከማልገልቹ  የኦህዴድ ብልጽግና ነን ይላል፤

፭ ጃልመሮ ደግሞ ራሱን ኦንግ ሲል ይጠራል።”

ስልቻ ቀልቀሎ፤ ቀልቀሎ ስልቻ…” መሆኑ ነው።

Filed in: Amharic