>

በባልደራስ ላይ የተከፈተውን የሐሰት ዘመቻ አስመልክቶ የተሰጠ ማሳሰቢያ...!!!

በባልደራስ ላይ የተከፈተውን የሐሰት ዘመቻ አስመልክቶ የተሰጠ ማሳሰቢያ…!!!

ሰሞኑን በመንግሥት ደህንነት እና  ፖሊስ፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ የብልጽግና ደጋፊ አክቲቪስቶች በሚዘውሯቸው የሶሻል ሜዲያ አውታሮች፣ ባልደራስን የጥፋት ኃይል አድርጎ ለመሳል የተወጠነ የሚመስል፣

በባልደራስ አስተባባሪነት የስሪላንካ መሰል ህዝባዊ አመጽ  እንደሚኖር  ተደርጎ ተናፍሷል፣ እየተናፈሰም ይገኛል። ሰሞኑን በመንግሥት ደረጃ የተለያዩ አካላትን ሰብስቦ  ይህንኑ እስከመናገርም ተደርሷል።

እንደሚታወቀው፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ፤  ከአመሰራረቱ ጀምሮ በህዝብ ጥያቄ፣ አደራ እና ኃላፊነት የተቋቋመ፣ ህጋዊ መሠረት ያለው የፖለቲካ ድርጅት ነው።

የባልደራስ አባላት የህወሓት/ኢሕአዴግ አምባገነናዊ  ስርዓት  ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ  ለማላቀቅ ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉ፤  ለ30 ዓመት የዘለቀ ሰላማዊ ትግልን ሲያስተማሩና ሲመሩ የነበሩ ናቸው።

ባልደራስ በቆመለት ዓላማም ቢሆን፤  በዲሞክራሲ መሰረታዊ መርህዎች የተቃኘው የፖለቲካ ትግሉ፣ በህግ ማእቀፍ ውስጥ የሚቀረጹና የሚስተናገዱ ሰላማዊ የሆኑ ማናቸውንም ዓይነት ሰላማዊ  የትግል ዘዴዎች እና የትግል ስልቶችን የሚከተል ነው።

በዚህም አካሄዱ አስፈላጊውን መስዋዓትነት ሁሉ እየከፈለ ትግሉን እያራመደ ያለ ብቸኛው ድርጅት ነው። ይህም በህዝብ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነትን አስገኝቶለታል።

በመሆኑም፣ ባልደራስ ከህዝብ የተሰወረ፣ በህዝብ  የማይታወቅ፣ በድብቅ የሚያከናውነው አንዳችም እንቅስቃሴ እንደሌለው ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን።

ሐምሌ 16 2014 ዓ.ም.

ባልደራስ ለእውነኛ ዲሞክራሲ!!

Filed in: Amharic