ሱማሌ ክልል ላይ ወረራ የፈፀመው አልሸባብ ነው ካልክ፤ የፖ*ካ ሀሁ አልቆጠርክም ማለት ነው!!
ቬሮኒካ መላኩ
የሱማሌ ክልልን ለመውረር በ13 መኪና ተጭኖ ”አቶ” ሁልሁል ላይ የደረሰው ሀይል አልሸባብ አይደለም፤ ለዚህ ማስረገጫው ደግሞ የልዩ ሀይሉ አባላት ከበባ ውስጥ አስገብተው ከሸኟቸው በኋላ በታጣቂዎቹ የተያዘው መታወቂያ እና የሰዎቹ ማንነት ነው፤ በነገራችን ላይ ይህ ሀይል ከጎረቤት ሀገር የመጣ ነው፤ ታዲያ የET ድንበር ጥሶ ሲገባ መጀመሪያ መከላከል የነበረበት ሀይል መከላከያ መሆን ነበረበት። ይሔም ሲሆን አልታየም!! ሌላውና ነገሩን ሁሉም በጥርጣሬ እንድናየው ያደረገው ክስተት ደግሞ የሱማሌ ብልፅግና ሽመልስን ፈርቶ ለ3 ቀናት ስለጉዳዩ ሳይተነፍስ መቆየቱ ነው። ወረራ በተጀመረ በማግስቱ መረጃውን ይፋ ያደረገው የጎረቤት ሀገር ሱማሊያ ሚዲያ ነው። እስከዛሬዋ ቀን ድረስ የፌደራል መንግስት ይፋ የሆነ መግለጫ ሲያወጣም ሆነ ሀገርን ከወራሪ ሲከላከሉ ለተሰው የሱማሌ ልዩ ሀይል አባላት ሀዘኑን ሲገልፅ አልታየም።
እነዚህን ሁሉ premises ስናሰባስበቸው አንድ ጥቃቱን ያደረሰው አልሸባብ ከሆነ በET መንግስት ይሁንታ እንዳገኘ ያሳያል!! ይህ ካልሆነ ደግሞ በአልሸባብ ካባ ለመጫወት የሞከረው የብልፅግናው አልሸባብ ነው ማለት ነው!