>

የዛሬው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍርድ ቤት ውሎ......!!!   (ታሪኩ ደሳለኝ)

የዛሬው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍርድ ቤት ውሎ……!!!

ታሪኩ ደሳለኝ


በመንግስት ፍቃድ ያላቸውን መፅሔት፥ ጋዜጣ አና ማንኛውንም አይነት መፅሐፍ እንዲያገኝ ፍርድ ቤት ወስኗል

የዛሬው ቀጠሮ አዲስ አበባ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የድርጀቱን ጉዳዮች በተመለከተ በአካል የግዴታ መገኘት እና መፈረም ለሚገባው ጉዳዪች አዲስ አበባ ፖሊስ  ይዤ አልሄድም የእጀባ አገልግሎትም አልሠጥም በማለቱና ተመስገን ከታሠረ ጀምሮ በመንግስት ፍቃድ ያላቸውን (ቴሌቭዥንና ራዲዮ)  መፅሔት፥ ጋዜጣ አና ማንኛውንም አይነት መፅሐፍ እንዳያገኝ በመከልከሉ ተመልክቶ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ነበር::

ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 18/2014ዓ.ም ልደታ 1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ሁለት ውሳኔወሸችን ወስኗል::

ውሳኔ

1ኛ  አዲስ አበባ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በአካል የግዴታ መገኘት እና መፈረም ለሚገባው ጉዳዪች  የእጀባ አገልግሎትም እንዲሰጥ

2ኛ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከታሠረ ጀምሮ በመንግስት ፍቃድ ያላቸውን  መፅሔት፥ ጋዜጣ አና ማንኛውንም አይነት መፅሐፍ እንዲያገኝ እንዳይገባ  ፖሊስ የከለከለው ፍርድ ቤቱም  የማግኘት መብቱ ይጠበቅ በማለት ውሳኔ ወስኗል::

ጋዜጠኛ  ተመስገን ደሳለኝ  እስር ቤት ከሆነ ዛሬ ስልሳ ቀኑ ነው (ሁለት ወሩ ነው)

ፍትህ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ 

Free journalist Temsegende Dsalegn

Filed in: Amharic