>

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት ሚኒስትርን "ከድጡ ወደ ማጡ አስግብተውታል...!!!”  (የኢትዮዽያ ሌክቸረርስ ድምፅ )

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት ሚኒስትርን “ከድጡ ወደ ማጡ አስግብተውታል…!!!”

 

 የኢትዮዽያ ሌክቸረርስ ድምፅ (Voice of Ethiopian’s Lecturers)


የዩኒቨርስቲ መምህራኑ ድምፅ ይፋ ባደረገው ግምገማው፣ ” በትምህርት ዘርፍ ላይ ያለው ባለሙያ ለሙያቸው ክብር እንዳይሰጡና በሙያቸው እንዲሸማቀቁ፤ሴክተሩን ለቀው ወደ ሌላ ሴክተር እንዲፈልሱ ሲደረግ ይስተዋላል”ብሏል።

እንዲሁም፣ “ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ሲመጡ ብዙ የዩኒቨርሲቲ መምህራን አዲስ ለውጥ ጠብቀው ነበር። ግን፣ እንኳን ተስፋ ሰጭ የሆነ አዲስ ነገር ልናይ ቀርቶ፣ ድሮም በችግር የተተበተበውን ትምህርት ሚኒስቴር  ከድጥ ወደ ማጡ አስገብተውታል።ለመምህራን የሚገባቸውን ክብርና ጥቅም ሳይሰጡ ስለ ትምህርት ጥራት ማውራት ተረት ተረት ይሆናል” በማለት፣ መምህራን የዕለት ጉርሳቸውን የሚሸፍኑበት ደምወዝ እያገኙ አለመሆናቸው ከፍተኛ የሰው ኃይል እያሳጣው ነው ብሏል።

መምህራን ለመጪው ነሃሴ 5 2014 ዓ. ም የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እቅድ ይዘዋል። ይህን አስመልክተው በ የኢትዮዽያ ሌክቸረርስ ድምፅ ፌስቡክ ላይ አስተያየት የሰጡት የበሌ ሁራ ዩኒቨርስቲው መምህር ሞገስ አስፋዬ፣ “የስራ ማቆሙን እና የሰላማዊ ሰልፉን ፕሮግራም በተመለከተ፣ ከነሃሴ 5 2014 ዓ.ም  ወደ መስከረም 2015 ዓ.ም ይራዘም ዓይነት ጩኸትን እየተመለከትኩኝ ነበር።

የእነዚህን ሃሳብ ሰጭ ሰዎች የግል profile (በፌስቡክ) ስዳስስ፣ አንድም፣ በደማችን እና ላባችን የሚቀልዱ የመንግስት ቅልብተኛ ካድሬዎች ናቸው፧ አለዚያም ፣የክረምት ተማሪዎች ሆነው የትምህርት ፕሮግራማቸው እንዳይስተጓጎልባቸው የሚሹ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።

እርግጠኛ ነኝ፣ ክረምት ለእረፍት የሚሄደው መምህር 10% አይሞላም።  ያ ማለት ሰላማዊ ሰልፍ ወይም የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንቅፋት አይሆንም።

በአጠቃላይ፣ ነሃሴ 5/2014 ዓ.ም በወጣው መርሃግብር ነገሮችን proceed  ማድረጋቸው የትግላችን empowerment አንዱ መንገድ ይሆናል እንጂ፣ በምንም መመዘኛዎች የትግል እንቅፋት አይሆንም” ብለዋል።

የዩኒቨርስቲ መምህራኑ፡ ጥያቄያቸው ሙሉ ለሙሉ የመብት ማስከበር እንጂ፣ ፓለቲካዊ ይዘት እንደሌለው አፅእኖት ሰጥተው ይናገራሉ። ጥያቄውን ያነሱት መምህራን የተለያየ የፖለቲካ እምነት ያላቸው ናቸው።

Filed in: Amharic