>
5:13 pm - Tuesday April 20, 1126

ከፌድራል የፀጥታ እና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠው  በክህደት የተሞላው  መግለጫ    ....!!!

ከፌድራል የፀጥታ እና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠው  በክህደት የተሞላው  መግለጫ    ….!!!

የፌድራሉ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ትላንት ያወጣው መግለጫ በአብዛኛው ሐሰት እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለፁ።

ሐሰቱ የሚነሳው፣ በወለጋ የተጨፈጨፉት አማራዎች መሆናቸውን በመካድ ነው ያሉት ምንጮች፣ ግብረ ኃይሉን በበላይነት የሚዘውሩት ኦህዴዶች፣ ሟቾችን “ንፁሃን ናቸው” በማለት ብቻ እንዲገለፁ አድርገዋል ብለዋል። ለኦነግ/ሸኔ ጥብቅና የቆሙት ኦህዴዶች ዋነኛ መለያ አማራ በተጨፍጫፊነት እንዳይገለፅ ባላቸው የከረረ አቋም እንደሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ።

ግብረ ኃይሉ ባወጣው መግለጫ፣ “ከሰኔ 07 እስከ ሐምሌ 07 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደ ዘመቻ ከ153 በላይ የሽኔ አባላት ተደምስሰው፣ ከ900 በላይ ተማርከውና በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየተጣራ ይገኛል” ያለው፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ውስጥ ያሉ የሸኔ ሰርጎ ገቦች ምን ያህል መንግስታዊ ከለላ እንዳላቸው አጋልጧል ብሏል። በመግለጫው ሰርጎ ገቦቹ እንደ ችግር እና አደጋ አልተጠቀሱም።

እንደሚታወቀው፣ ከጭፍጨፋው የተረፉት ሁሉ በጫካ ካለው ኦነግ/ሸኔ ይልቅ በክልሉ መስተዳድር ባለስልጣናት የሚደርስባቸው ጉዳት እንደሚያመዝን በተደጋጋሚ ይናገራሉ፣ እየተናገሩም ይገኛሉ። በክልል ደረጃ ላሉት የኦነግ/ሸኔ ሰርጎ ገቦች(ፈረንጆቹ fifth columnists የሚሏቸው) በፌድራል ደረጃ ሥልጣን ላይ ያሉት ሰርጎ ገቦች ከለላ እንደሚሰጡም ይታወቃል። በግብረ ኃይሉ መግለጫ የታየው ይህ እውነታ ነው ብለዋል ምንጮቻችን።

መግለጫው እንደ ወትሮው በፋኖ ላይ ሀገር የሰለቸውን የሐሰት ውንጀላ በመሰንዘር ፣ “እርምጃ የተወሰደባቸው የፋኖ አባላት፣ የንፁሃን ዜጎችን ህይወት እያጠፉ፣ ከቤት ንብረታቸው እያፈናቀሉና እየዘረፉ የነበሩ፣ ከክልና ከፌደራል የፀጥታ አካላት የከዱ፣ በግድያ ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ፣ በጥቅሉ 5 ሺህ 804 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል” ብሏል።

እውነታው ግን፣ ከተያዙት መካከል በተዘረዘሩት ወንጀሎች የሚጠረጠሩት በመቶዎች እንኳን የሚቆጠሩ እንዳልሆኑ ምንጮቻችን ይናገራሉ።

ከፋኖ ጋር የተያያዘው እውነተኛ ምክንያት፣ በዚያው በመግለጫው፣ “የፅንፈኛው ፋኖ ቡድን አባላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከፖሊስ ተቋማት ዕውቅና ውጪ ወጣቶችን  በመመልመል፣ ያሰለጥናሉ፣ የጦር መሳሪያ ያስታጥቃሉ” የተባለው ነው የሚሉት ምንጮቻችን፣ ይህ ሂደት መንግሥት ከአወጀው የክተት ጥሪ ግዜ አንስቶ የነበረ ፣ ጦርነቱ እንዳለቀ በመንግሥት እስካልታወጀ ድረስ ህጋዊ አካሄድ እንደሆነ ያስረዳሉ። የመንግሥት ፍላጎት ፋኖን ሚሊሺያ ማድረግ እንደሆነም ይናገራሉ።

በመጨረሻም፣ በመግለጫው፣ “ወደ አዲስ አበባ ሰርገው በመግባት የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነበሩ 51 ጽንፈኛ የፋኖ አባላት፣ በከተማው ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ(የአዲስ አበባ ወጣቶች) በቁጥጥር ስር ውለዋል” ያለው በሐሰት የተወነጀሉ ንፁሃን መሆናቸውን፣ የኦህዴዶች ፍላጎት  ህዝቡን አንገት አስደፍቶ ከተመዋን በአስተዳደር የኦሮሚያ አካል ማድረግ፣ አማርኛን ማዳከም፣ የከተማዋን የብሄርና የኃይማኖት ስብጥር መቀየር፣ በከተማዋ የኦህዴድ ባለሥልጣናት፣ ዘመዶቻቸውን እና ኔትወርካቸውን ያማከለ አዲስ ባለሀብት መፍጠር እንደሆነ ምንጮቻችን አበክረው ይናገራሉ።

ባልደራስ

Filed in: Amharic