>

ዘመቻ ፍትሕ ...!!! (ታሪኩ ደሳለኝ)

ዘመቻ ፍትሕ …!!!

ታሪኩ ደሳለኝ

ህወሓት፣ ጥቅምት 24/2013 የሰሜን ዕዝን ከጀርባው በመውጋት ጦርነቱን ከጀመረ በኋላ በነበሩ ጊዜያት ጋዜጠኛ ተመስገን በሙሉ የኃላፊነት ስሜት የጦርነት ጊዜ የመረጃ ትንተናዎችን ወደአንባቢያን ሲያደርስ ቆይቷል፡፡

ጦርነቱ በጀመረ በአምስተኛው ቀን የወቅቱ ኢታማዡር በነበሩት ጀኔራል አደም መሀመድ ቢሮ ተጠርቶ፣ ከዚህ ቀደም የነበሩ የሀሳብ ልዩነቶች ወደጎን ተትተው በጦርነቱ ጉዳይ ‹አግዘን› የሚል ጥሪ እንደቀረበለት ስናስታውስ ጋዜጠኛ ተመስገን፣ የመከላከያ ጠበቃ የመሆኑን እውነታ በጭንቁ ጊዜ ቁልፍ አመራሮች ሳይቀር እንደመሰከሩለት አስረጅ ሆኖ ይቀርባል፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ጦርነት (በጥቅምት 24ቱ) ሕወሓት በህይወት እንዲቆይ መፍቀዱ፣ አገር የሚሸነሸንበትን ካራ በፍላጎት እንደማቀበል ነው፡፡ በየትኛውም ሚዛን አንድ የክልል አስተዳደር፣ ለመላ አገሪቱ ፍርሰት ጠንቅ እስኪሆን ድረስ የሚተውበት የተፈጥሮም የሕግም ፍቃድ እንደሌለ በማስታወስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር ከማይታረም ስህተት ራሱን እንዲጠብቅ ደጋግሞ ወትውቷል፡፡የሀገረ-መንግሥቱ ዘብ የመሆን ብሔራዊ ተልዕኮ ያነገበው የመከለከያ ሠራዊቱ በመጀመሪያው ምዕራፍ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት ቢወጣም፤ ከጀርባ የወጉትን ከሃዲያን ከፊት ለፊት በመደምሰስ የከሃዲያንን መጨረሻ በተግባር ቢያሳይም፤ በሰለጠነበት ሙያ አጥንቱን ከስክሶ፣ ደሙን አፍስሶ አገርና ሕዝብን ቢያስከብርም፤ ሠራዊቱ በነፍሱ ተወራርዶ ያመጣው ድል፣ በቀሽም-ፖለቲካና በፈዘዘ-ዲፕሎማሲ መቀልበሱ የፖለቲካ አመራሩን የሚያስተች ነበር፡፡ ፡ መቼም ወታደር ለግንባር እንጂ፣ ለፕሮፓጋዳ እንደማይሰለፍ ይታወቃልና፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ‹ሰራዊቱን አታስወጉት!› በሚል አመራሩን መተቸቱ ጥርስ እንዳስነከሰበት የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

ግልባጭ፦

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ

ለመገናኛ ብዙሐን ባለሞያ ማህበራት

ለጋዜጠኞችና ለማኅበረሰብ አንቂዎች

ለሲፒጄ

ለአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ አበባ

ለአውሮፓ ሕብረት

ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል

በአዲስ አበባ ላሉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት

#ዘመቻ_ፍትሕ

#ፍትህ_ለጋዜጠኛ_ተመስገን_ደሳለኝ

#free_journalist_Temsegen_desalegn

Filed in: Amharic