>

የአዲስ አበቤው ቢኒያም ታደሰ ስቃይ! (ናትናኤል የማነህ)

የአዲስ አበቤው ቢኒያም ታደሰ ስቃይ!

ናትናኤል የማነህ


ቢንያም ሲያየኝ ወደ ፈጣሪ እንጋጦ ” እንኳን በህይወት አገኘዋቹ ” እያለ እንባ አይኑ ላይ ግጥም አለ ፤ እማይሆን ስሜት ውስጥ ገባን የደረሰበትን ግ*ፍና በደ*ል ሲነግረኝ ፤ ስው ግን እንዴት በሰው ስ*ቃይ ይደሰታል ? ምን አይነት አው*ሬነት ነው ? ስንት አይነት ሰው አለ፤ ሰው በሰው ቁ*ስል ላይ ጨው እየነ*ሰነሰ እንዴት ይዝናናል እያልኩ ምን እንደሚያስደስታቸው ማወቅ አቃተኝ!!

ቢንያምና ብዛት ያላቸው አዲስ አበቤዎች አዎሽ 7 እንደገብ  በሁለት ቤት ውስጥ የታሰሩ ሲሆን ፤ አንዱ ቤት ሰማንያ፣  አንዱ ቤት ሰባ የሚጠጉ እስረኞች ነበሩ !! ለ15 ቀን የሚሆን በቀን ሶስት ዳቦና አንድ ኩባያ ውሃ ጋር ይቀርብላቸው ነበር ምሳ ቁርስ እራት መሆኑ ነው እንግዲ !!

ከዛ ተሻሻለ ተብሎ ቁርስ 1ዳቦ በሻይ ፣ ምስና እራት ሁለት ሁለት ዳቦ በወጥ መቅረብ ጀምረ፤  ሌላ አስቃቂው ነገር በ45 ቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር ገላቸውን መታጠብ የቻሉት አብዛኛዎቹ እስረኞች ቅያሬ ልብስ እንኳን አልነበራቸውም!!

ከታሰሩበት ክፍል መውጣት የሚችሉት ሽንት ቤት መሄድ ሲፈልጉ ብቻ እንደሆነ አስረድቶኛል ። እንደዛም ሆኖ ቢንያምን አልሰበ*ሩትም ገራሚና ጠንካራ መሆኑን በዚም መከራ ውስጥ ሆኖ አሳይቷቸዋል !!

ቢኒ ለእስክንድር ያለውን ፍቅር እናውቀዋለን፤ “አባቢ ሰላም ነው አይዞ በርታ በለው” ሲለኝ ምን እምመልስለት ጠፋኝ “ደህና  ነው አንተ ብቻ በርታ” ብየው ከጠበቃ ቤተማርያምና ከይድነቃቸው ጋር እንዲያወራ ገለል አልኩ ከነሱም ጋር የልብን አውርቶ በሰላም ተለያይተናል !!

መጠየቅ ለምትፈልጉ ከሰኞ እስከ ሰኞ በሥራ ሰዓት መጠየቅ ይቻላል !!

ፍትህ ለአዲስ አበቤዎች ፍትህ ለቢንያም ታደስ!!

Filed in: Amharic