>

ፊሽካ ብቻ እየተጠበቀ ነው…!! (ዘመድኩን በቀለ)

ፊሽካ ብቻ እየተጠበቀ ነው…!!

ዘመድኩን በቀለ

“…ህወሓት የቀበረችውን ታንክ፣ የዘረፈችውን የሃገር መከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ፣ በምርኮ ስም በስጦታም የተሰጣትን ወታደራዊ ቁሳቁስ ሸክፋ ለመጨረሻ ጊዜም ባይሆን የዓለምን ትኩረት ለመሳብ፣ የውስጥ ትኩሳቷንም ለማብረድ፣ የዳያስጶራውንም መፋዘዝ ለማነቃቃት፣ በዚያውም የተዘጋጋውን በር ለማስከፈት ወደ ጦርነት ለመግባት ወስናለች። ከኤርትራ፣ ከዐማራ፣ ከአፋርና ከሃገር መከላከያ ጋር ለመግጠም ነው ጉዞዋ።

“…ለውጊያ የሚሆነውን በጀት በኢትዮጵያ ስም የኦሮሙማው መንግሥትና የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ስፖንሰር አድርገዋታል። ነዳጅ በሚልዮን ሊትር ገብቷል። መድኃኒት፣ ስንቅና ትጥቅም እንዲሁ ገብቶላታል። ወታደሩን ማመላለሻ ከባድ መኪኖችም የእርዳታ እህል እንደጫኑ ገብተው በዙያው ቀርተዋል። የትራንስፖርት ችግርም የለባትም።

“…በሌላ በኩል ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትግራይ ወደ ዐማራ ክልል የሚሰደደው ህዝብም ከወትሮው በተለየ መልኩ ህወሓት እንዴት እንደፈቀደችላቸው ባይታወቅም ስደተኛው በገፍ ጨምሯል።

“…የዐማራ ልዩ ኃይልም በራያ ግንባር በገፍ ገብቷል፣ እየገባም ነው። የሚገርመው ግን ለጥቂት ዓመታት ጥሎት የነበረውንና ህወሓት አሰፍታ የሰጠችውን የሽንት ጨርቅ ባንዲራዬ ብሎ የሚያውለበልብ የዐማራ ሰራዊት ነው ወደ ግንባር እየተመመ ያለው። ከወዲያ ማዶም ከወዲህ ማዶም አንድና ተመሳሳይ ባንዲራ ይዞ መዋጋቱ ግን ይደብራል። ዐማሮቹ የህወሓትን ባንዲራ ለህወሓት መልሳችሁ እናንተ የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዛችሁ ብትሰለፉ ነው የምመክራችሁ። ለሞራላችሁም ጥሩ አይደለም። እርግጥ ነው ብአዴን አፍቃሬ ህወሓት ነው ቢሆንም ግን ደስስ አይልም። ባንዲራውን ለመርዞ ተውላት። የቀረውን የቪድዮ ዘገባ ነገ መረጃ ቲቪ ላይ ጠብቁኝ።

 

Filed in: Amharic