የ100 እና የ30 ሺህ ብር ዋስ ተፈቅዶላቸው የከፈሉ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬም ተጨማሪ 7 ቀናት ተሰጠባቸው …!!!
*…. አቶ ስንታየሁ በጠና ታመዋል
* … ከአዋሽ ሰባት ወደ አባሳሙኤል እስር ቤት የመጥ እስረኞች መልክት!!
ዛሬ ነሐሴ 16/2014 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርበው የነበሩት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለነሀሴ 23/2014 ዓ.ም ተቀጥረዋል።
በመጀመሪያ በባህርዳር ከተማ፣ በመቀጠል በፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ሚክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ምርመራ ታስረው የነበረ መሆኑ ይታውሳል። በሁለቱም እስሮች የ30ሺህ ብር ዋስ እና የ100 ሺህ ብር ዋስ ተፈቅዶላቸው የከፈሉ ቢሆንም አፈኙ የኦህዴድ ብልፅግና አቶ ስንታየሁ ታስረው ከነበረበት አባ ሳሙኤል ማረሚያ ሲወጡ በር ላይ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ደግመው በኃይል በመያዝ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አስረዋቸዋል።
ከእስሩ በተጨማሪ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በኩላሊት ህመም እና በደም ግፊት ተይዘው እየተሰቃዩ ይገኛል። በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ስር በነበሩበት ግዜ በፖሊስ ሆስፒታል የነበራቸው የህክምና ክትትልም በአሁን ሰዓት ተቋርጦባቸዋ።
በእሁኑ ሰአት አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ ታስረው ይገኛሉ።
በተያያዘ:-
ከአዋሽ ሰባት ወደ አባሳሙኤል እስር ቤት የመጥ እስረኞች መልክት!!
ከአዋሽ ሰባት ወደ አዲሰ አበባ ስንመጣ፤ ብዛታችን 45 ነበር። ከዚህም ውስጥ ሁለት ሴቶችን ሜክሲኮ ወደ ሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ፣ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ወሰዷቸው። የቀረነው – 43ታችን ደግሞ፣ ጠያቂም ሆነ አስታዋሽ አጥተን፣ ፍርድ ቤትም ሳንቀርብ፣ መርማሪ ፖሊስ ሳያናግረን እስካሁን በአባ ሰሙኤል እስር ቤት ታጎረን አለን። አሁን ወደ ሜክሲኮ የፌዴራል ፖሊስ ቢሮ እንደምንወሰድ ቢነገረንም፣ ግልጽ ምክንያቱን ግን እንድናውቀው አልተደረገም። በዚህ አጠቃላይ ሁኔታ ውስጥ አደጋ ላይ ነን። ወዴት ሊወስዱን እንደሚችሉም አናውቅም። ሕይወታችን አደጋ ላይ ነው። ፍትሕ የሌለበት አገር ላይ፣ የግለሰብ እስረኛ ሆነናል። ስለዚህ ሁላችሁም፣ ስለእኛ የሚገዳችሁ በሙሉ፣ ድምፅ ትሆኑን ዘንድ እንጠይቃችኋለን።