>

ድርድሩ እንዲሳካ መደረግ  ያለበት ሁሉ መደረግ አለበት....!!! (ግርማ ካሳ)

ድርድሩ እንዲሳካ መደረግ  ያለበት ሁሉ መደረግ አለበት….!!!

ግርማ ካሳ 

ወያኔ በጦርነት ምንም ነገር አታሳካም፡፡ ብዙ ጊዜ ሞክራ አልቻለችም፡፡ ህወሃትን በጦርነት ማሸነፍና የትግራይ ህዝብን ነፃ ማውጣት ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግን በአብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ አዝማችነት፣ በነርሱ ዕዝ ስር የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ሰዎቹ ሕወሃት ታሪክ እንድትሆን ስለማይፈልጉ፣  ጫፍ ከተደረሰ በኋላ ተመለሱ ብለው ድሉን መቀልበሳቸው አይቀርም፡፡ የሚቀለበስ ድል ደግሞ ማሸነፍ አይሆንም፡፡

ስለዚህ ወደ ጦርነት መሄድ፣ ትርፉ የአማራንና የትግሬ ወጣቶች ማስጨረስ ፣ የህዝቡን ስቃይና መከራ ማራዘም ፣ አገርን ማውደም ብቻ ነው፡፡

ጦርነት መደረግ የለበትም፡፡ አሸንፎ፣ ጦርነቱን በቶሎ መቋጨት ቢቻል አንድ ነገር ነበር፡: ግን አይቻልም፡፡ ስለዚህ ዋጋና እርባና ለሌለው፣  senseless ጦርነት አገርና ህዝብ መከራ ውስጥ እንዲዘፈቀዱ መደረግ የለበት፡፡ ትግራይ ያሉት ለነ ዶር ደብረጽዮን፣ አማራ ክልል ያሉት የብልግናዎችን ስልጣን ለማራዘም ደማቸውን ማፈሰስ የለባቸውም፡፡

ወደ ድርድሩ ስመጣ የአፍሪካ ህብረት ይሁን አይሁን በሚል ውዝግብ አለ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ጥርስ የለውም፡፡  ከአፍሪካ ህብረት ይልቅ አሜሪካ መግባቷ ነው ጥቅም የሚያመጣው፡፡ ለዚኦህ ነው በድርድሩ አሜሪካኖች መግባት አላባቸው የሚል አቋም ያለኝ፡፡ አሜሪካ ብቻ ናት ወደ ጦርነት እንዳይኬድ እነ አብይን በኢኮኖሚ እቀባ  ህወሃቶችን በውጭ በልጆቻቸውና ዘመዶቻቸው ስም ያላቸው የባንክ አካውንት በማገድ፣ መቆንጠጥ የምትችለው:፡ አሜሪካ ጣልጋ ከገባች ነው ጥሩ ነገር ሊፈጠር ይችላል፡፡

ህወሃቶች ወልቃይት ወልቃይይ ይላሉ፡፡ ወልቃይትን እንደ ሰበብ ነው የሚጠቀሙት፡፡ ሰላም እንዳይመጣ ለማድረግ ወልቃይትን እንደ አንድ መሳሪያ ነው እያቀረቡ ያሉት፡፡ አንድ ነገር ግልፅ ላድርግ ፣ በወልቃይት ጉዳይ ሆነ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን ሁሉንም አሸናፊ ባደረገ መልኩ መፍታት ይቻላል:: በትግሬውና በአማራው መካከል: በህዝብና በህዝብ መካከል ችግር የለም””

ችግር ያለው፣  ኢህአዴግ ሆነው ህዝብን ለሰላሳ አመታት በአንድ ላይ መከራ ሲያሳዩ የነበሩ፣ አሁን እርስ በርስ በስልጣን ተከፋፍለው እንደ ጠላት የሚተያዩ፣  የዘር ፖለቲካ አራማጆች: ህወሃቶችና ብልፅግናዎች፣  ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ለስልጣናቸው ስለሚያስቡ ነው::

Filed in: Amharic