ብልጽግናዎች ማለቂያ በሌለው ጥያቄያቸው የኦሮሞ ህዝብንም ችግር ውስጥ ከተውታል…!!!
ማዕዛ መሐመድ
*… ዛሬ ሙሉዋን አዲስ አበባን ቢወስዱ፣ ደብረብርሃንን ይመኛሉ! ደብረብርሃንን ብትሰጣቸው፣ ደሴን ይጠይቃሉ! ደሴን ብትሰጣቸው፣ መቀሌን ይጠይቃሉ…!!!
የብልፅግናዎች ጥያቄ ማለቂያ የለውም። አዲስ አበባን ቆርሰው ወስደውም አልበቃንም እያሉ ነው። እኛ ቱሉ ዲምቱንና ኮዬ ፈጬን ሳይሆን አዲስ አበባን ነው የፈለግነው ብለዋል።
የሚገርመው ማለቂያ የሌለው ጥያቄያቸው አዲስ አበባን ቢወስዱ፣ ደብረብርሃንን ይመኛሉ። ደብረብርሃንን ብትሰጣቸው፣ ደሴን ይጠይቃሉ። ደሴን ብትሰጣቸው፣ መቀሌን ይጠይቃሉ።
ይሄንን ማለቂያ የሌለው ጥያቄያቸውን ለማስተናገድ ደግሞ መንግስታዊ ሽብር ይፈጥራሉ። ህዝቡን ያሸብራሉ። ይገድላሉ፣ ያስገድላሉ። በአጠቃላይ ህዝቡ ሰላም አጥቶ ጭንቀት ውስጥ ሲገባ የፈለጉትን ይወስዳሉ። ግርግር ለሌባ ይመቻልና በግርግር ትርፍ ያገኛሉ።
አሁን የአማራና የትግራይ ህዝብ ችግር ውስጥ ነው፣ ስለ አዲስ አበባም፣ ስለ ኢትዮጵያም የሚያስብበት አይደለም። even የኦሮሞ ህዝብም ችግር ላይ ነው።