>
5:29 pm - Thursday October 10, 1935

 ወገን ሆይ ወያኔና ብልጽግና እንዴት ተናበው ድራማውን እየተወኑት እንደሆነ ልብ በል!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን) አርጋው

 ወገን ሆይ!  ወያኔና ብልጽግና   እንዴት ተናበው ድራማውን እየተወኑት እንደሆነ ልብ በል‼

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እያንዳንዷን ነገር እየተናበቡ ነው የሚያደርጓት‼ 

🔹 Patternኑን ልብ ብላቹህ ካያቹህት ልክ ባለፈው ያደረጉብንን ድራማ ወይም የሴራ ጦርነት ስልትና አፈጻጸም ነው አሁንም እየደገሙት ያሉት‼

• ይሄኛው ዙር የአሻጥር ጦርነት የድራማው መጨረሻ መሆኑን ብታውቁ መልካም ነው!

ድራማው ከመጠናቀቁና ወያኔ “አሸነፈ!” ተብሎ አራት ኪሎ ከመግባቱ በፊት ግን ወሎንና ጎንደርን ብቻ ሳይሆን ጎጃምንና ሸዋንም በወያኔ እጅ በመጣል ሕዝቡ መከራን ተሰቅቆ፣ በእጅጉ ተዳክሞ፣ በእጅጉ ተማሮና ተሰላችቶ ለወያኔ እጅ እንዲሰጥ፣ ወያኔን አምኖ እንዲቀበል፣ “በቃ እንደፈለገ ያድርግ!” እንዲል ይደረጋል‼

ልብ በሉ አማራ እንዲህ እስኪል ድረስ ወያኔ አማራን አልፎ ወደመሀል እንዲቀጥል አይደረግም‼

አማራን እንዲህ ካደረጉ በኋላ ግን ተራው የሌላው ይሆናል‼

ሌላውም እንደዚሁ መከራን ተሰቅቆ፣ በእጅጉ ተዳክሞ፣ በእጅጉ ተማሮና ተሰላችቶ ለወያኔ እጅ እንዲሰጥ፣ ወያኔን አምኖ እንዲቀበል፣ “በቃ እንደፈለገ ያድርግ!” እንዲል ይደረጋል‼

ይሄ ብቻ ሳይሆን ወያኔ ከዚያ በኋላ ለክፍለ ዘመናት ያለ ኮሽታ ተደላድሎና ተመቻችቶ መግዛት ስለሆነ ፍላጎቱ በብልጽግና ስም ሰብስቦ ከያዘው የየብሔረሰቡ ኤሊት ውጭ ያለውንና “ሕዝብ ሊያሳምፅ፣ ሊረብሽ ይችላል!” የሚለውን የየብሔረሰቡን ኤሊት ክፍል ልቅም አድርጎ ድራሹን ያጠፋዋል‼

• አማራ ሆይ!እንዲህ አድርገው አብዛኛውን ሕዝብህን ጨፍጭፈው ፈጅተው ያንተ የሆነውን ሁሉ ከወሰዱ በኋላና የምትተርፈውንም አከርካሪህና ቅስምህ እንክትክት ብሎ ተሰባብሮ የዘለዓለም ባርነትን እንድትቀበል አድርገው ጥለው በቁምህ ገለው ሲቀብሩህ ዓይንህ ከሚያይ አሁንም ቢረፍድብህም አልመሸምና በመጨረሻ የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ወኔና ስሜት ተነሥተህ ወያኔን የተጣላ መስሎ እየተወነ አንተን አፍዝዞና አደንዝዞ፣ እጅና እግርህንም እግር ከወርች አስሮ ወደ መቃብርህ እየወሰደህ ካለው ከፀረ አማራው ብአዴንና ጭፍሮቹ ጀምረህ መጥረግህን ጀምር!!

ወገን ሆይ!እመነኝ ዝም ካልክ የሚጠብቅህ የሞት ሞት መሆኑን አውቀህ በራስህ ተማምነህና ቆርጠህና ጨክነህ ከተነሣህ የፈለገ ቢሆን ከሕዝብ ኃይል የሚበልጥ ኃይል ስለሌለ ታሸንፋለህ‼

• ከአማራ ውጭ ያለኸው ኢትዮጵያዊም አንተም ባለተራ መሆንህንና የተደገሰልህ ሞት መሆኑን በዚህም ምክንያት አማራጭ እንደሌለህ አውቀህ ከአማራ ጋር በመነሣት በየደጅህ በወያኔ/ኢሕአዴግ ወይም በብልጽግና ላይ ቆርጠህና ጨክነህ ዝመት‼

• የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!”እምቢ!” ካልክና “እልቂት፣ አስከፊ የዘለዓለም ባርነትና አጥንት ሰባሪ ውርደት ይሻለኛል!” ካልክ ግን የራስህ ጉዳይ!!

Filed in: Amharic