ስንታየሁ ቸኮል በ10 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ተወስኗል…!!!
ጌጥዬ ያለው
የስርዓቱ አስጨናቂ አቶ #ስንታየሁ ቸኮል ለ3ኛ ጊዜ በሀሰት የተከፈተበትን ምርመራ ለ3ኛ፤ በ3ኛው ፍርድ ቤት አሸንፏል። በ10 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ወስኗል።
ከዚህ በኋላ ‘ክልሎች’ ወይም ሚንስትር መሥሪያ ቤቶች እየተቀባበሉ ያስሩት ካልሆነ በቀር ከባሕር ዳር እስከ አዲስ አበባ ቅብብሎሹ ያለቀ ይመስላል¡ በርግጥ እነርሱ ምን ይሳናቸዋል፤ ከጎረቤት ሀገራት ጋርም ተቀባብለው ያስሩት ይሆናል እኮ¡ (አጋር ካገኙ ማለቴ ነው)
ስንትሽ ለዚህን ያህል ጊዜ በቅብብሎሽ ሲታሰር ለኩላሊት ህመሙ እንኳን ተገቢውን ህክምና አላገኘም። ይህ ሁሉ ሲሆን የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ተቋማት ያሉት ነገር የለም። በአንድ ፍሬ ነገር በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በፈረቃ ምርመራ ሲከፈትበት የሕግ የሙያ ማሕበራትም ሆኑ የሕግ ትምህርት ቤቶች ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው አልፈዋል።