የሰሜኑ ጦርነት እንዲያልቅ አይፈለግም – የዥዋዥዌ ጨዋታ ነው የያዙት …!
ግርማ ካሳ
ይሄ ተያዘ: ያ ተለቀቀ ለሚል ስሜታዊ ፕሮፖጋንዳ ጊዜ የለኝም:: ከዚህ ጋር በተገናኘ የማዘንና የመደሰት የዥዋዥዌ ጨዋታ ሰልችቶኛል::
ጥያቄዎቼ ተያዘ : ተለቀቀ የሚል ጨዋታ መቼ ነው የሚቆመው ? ጦርነቱ በድርድር ይሁን በአንዱ አሸናፊነት መቼ ነው የሚጠናቀቀው ? ትግራይ: ጎንደር: ወሎና እፋርም ያለው ህዝብ መቼ ነው ሰሳም የሚያገኘው ? የሚሉት ናቸው::
ወገኖች ዋናውና ትልቁ ተጠያቂው የብልፅግና መንግስት ነው::
1ኛ ብዙ ጊዜ በጦርነት ህወሃትን ሙሉ ለሙሉ ማሸነፍ ሲቻል ጫፍ ሲደረስ ተኩስ አቁሙ እያለ ህወሃትን ማዳን ብቻ ሳይሆን እንደገና እንድትጠናከር እድል የሰጠና የሚሰጥ መሆኑ ነው::
2ኛ ህወሃቶች ለድርድር ፍቃደኛ እንዲሆኑ : ቢያንስ ሁሉንም ባይሆን ግማሽ የጠየቁትን የአብይ መንግስት መሟላት ይችል ነበር:: መብራት: ኔትዎርክ የመሳሰሉት ማስጀመር ችግር አልነበረም:: ለህዝብ የሚያስብ መንግስት ቢሆን ኖሮ ህወሃቶች ሳይጠይቁ ማድረግ ነበረበት::
እነዚህን መሰረታዊ አገልግሎቶች ማሟላት ቢቻል ኖሮ ምን አልባትም ህወሃት ወደ ውጊያ እንዳትሄ ህዝቡም ጫና ያደርግ ነበር:: ህወህት ጦርነቱን እንዳያቆም ሰበብ ነው የሰጡት::
ነገር ግን የአብይ መንግስት በሰሜን ሰላም እንዲኖር የሚፈልግ አይመስኝም:: ትግሬውና አማራው እየተገዳደለ : ሰሜኑ በጦርንቱ ምክንያት እየቆረቆዘ: ህዝቡም እየደኸየ : እነርሱ ተረጋግተው በሸገር እየተምነሸነሹ ለመቀጠል ነው የሚፈልጉት::
የሚያሳዝነው ተጋሩዎችም አማራዎችም ይሄን መገንዘብ አለመቻላቸው ነው::ለነ ወልቃይት: ለነ ራያ ቀላል ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ መፍትሄ እያለ: እልህ ስላለ: መነጋገር ሲቻል መተላለቅ አሳዛኝ ነው:: በተለትም ህወሃቶች ጋር ያለው ግትርነት ነው ከአማራው ጋር መነጋገርን አስቸጋሪ ያደረገው::
አሁንም እላለሁ:: የአብይ አህመድ መንግስት በውሸት ላይ የተመሰረተ ነው:: ሆን ብሎ ድርድሩ እንዳይሳካ እንዲጏተት ሊያደርግ ይችላል:: ለምን በሰሜን ሰላም መምጣቱ ለስልጣናችን ያሰጋናል ስልሚሉ:: ነገር ግን ቅንነት በተሞላበት መልኩ ከአማራ ሃይሎች ጋር በተጏዳኝ መነጋገር ቢጀምሩ የተሻለ ውጤት ሊያመጡ ይችላሉ::