>

መሬት ያለው አሁናዊው እውነታ ...!!! (ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ )

መሬት ያለው አሁናዊው እውነታ …!!!

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 

<< ሕወሓት በራያ ግንባር ጦርነት ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ከፋኖዎች ጋር በምሽግ ውስጥ  ነበረኩ ። ጦርነቱ በየደቂቃው  ተለዋዋጭ በመሆኑ አንድ የጠራ ምስል እስካገኝ ድረስ ከመፃፍ ታቅቤ ቆይቻለሁ። >>

” ፋኖ ፣ መከላከያ ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ከራማ ኪዳነ ምህረት እስከ ጎብዬ ፣  በላጎ እና ቃሊም ድረስ  የሞት ሽረት ውጊያ እያደረገ ነው። ”

“ይሁን እንጅ አሁን በዚህ ሰአት የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የተወሰነው ሾልኮ  ከጎብዬ በእስከ ዱቡብ ምዕራብ በኩል ዱርለበስ  በሚባለው አካባቢ  የአላውሃን ወንዝ ለመሻገር እየተንደረደረ ነው። ይህ አቅጣጫ  በማመጫ ድጎ እየሱስ አድርጎ  ወደ ወልዲያ የሚያስገባውን  ዋሻው ለመዝጋት ነው። ”

” ጥምር ጦሩ ዋሻውን ቀድሞ ቢይዝ  ወልዲያን ማዳን ይቻላል የሚል መልዕክት አለኝ። ባሳለፍነው አመትም የሕወሓት ቡድን ይህንኑ መስመር ተከትሎ ወልዲያ መግባቱ የሚታወስ ነው። ”

“አማራ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕወሓት ሕዝባዊ ሆኖ እንደመጣው ሁሉ ሕዝባዊ ሆኖ ካልተነሳ በስተቀር አንድ ቀን ጧት በራችንን ስንከፍት ደጃፋችን ላይ እናገኛቸዋለን።”

ነቅተህ ፥ አንቃ! በትናትናው መንገድ ተጉዞ ድጋሜ መውደቁ ይብቃ!

Filed in: Amharic