>

አብይም መቀሌን ደብረጽዮንም አራት ኪሎን አይመኙም ፤ የሁለቱም የጋራ ፍላጎት አማራን ማድቀቅ ነው...! (ጌጥዬ ያለው) 

አብይም መቀሌን ደብረጽዮንም አራት ኪሎን አይመኙም ፤ የሁለቱም የጋራ ፍላጎት አማራን ማድቀቅ ነው…!!!

ጌጥዬ ያለው 

የትግሬ ወራሪ ሃይል ፍላጎት እምዬ ምኒልክ ቤተ መንግሥት መግባት አይደለም። ለዚህ የሚያበቃ አቅምም የለውም። ፍላጎቱ የአማራን አፅመ ርስቶች ወርሮ የራሱን ሽራፊ ሀገር መገንባት ነው። ለዚህ ገዥው ወራሪ ኦሕዴድ-ብልፅግና-ም ተባባሪ ነው።

ነገሩ አማራውን ነጣጥሎ የማጥቃት ስትራቴጂ ነው። ከዚህ ቀጥሎ አማራ ፈፅሞ እንዲጠፋና ግዛተ መሬት እንዳይኖረው ለማድረግ ይሠራል።

#መፍትሔው በነቂስ ወጥቶ ወራሪውን ምሱን ሰጥቶ መመለስ ነው። አማራ እስከ ጎብየ ተወሮ መዝመት አብይ አሕመድን መጥቀም የሚመስለው ካለ በግማሽ አንጎሉ የሚያስብ የእዕምሮ ስንኩል መሆን አለበት። የምስራቅ አማራ ፋኖ ድልድይ ተሰብሮበት ከበባ ውስጥ ሲገባ እያየ፤ ጦርነቱን ከመጤፍ ሳይቆጥር ለሰላማዊ የሥራ ጉብኝት አልጀርስ የገባውን ጠቅላይ ሚንስትር ተብየ እያሰበ ‘አልዘምትም’ ብሎ የሚያኮርፍ ካለ ‘እቤትህ እስኪመጡ ትግርኛ ተለማምደህ ጠብቃቸው’ ከማለት ውጭ ምን ይባላል።

ከልጅ እስከ አዛውንት፤ ከሽንኩርት ቢላ እስከ ቡድን የጦር መሳሪያዎች ይዞ በመውጣት የፊትንም፤ የኋላንም ጠላት መጥረግ ምትክ የሌለው መፍትሔ ነው።

Filed in: Amharic